Gubae

Eregnaye New

ሳምራዊት ሲዛር · Yene Aleme

እግዚአብሔር ፡ እረኛዬ ፡ ነው ሚያሳጣኝ ፡ የለም ፡ የማጣው ፡ የለም/2 እግዚአብሔር ፡ ፀጥታዬ ፡ ነው ሚያውከኝ ፡ የለም/3 የማመልከው ፡ አምላክ ፡ የተደገፍኩት ጠበቀኝ ፡ እንዳልጠፋ ፡ እኔ ፡ እንዳልሞት በእጆቹ ፡ መዳፍ ፡ ላይ ፡ ስለቀረፀኝ አልጠፋም ፡ የሚራራ ፡ አባት ፡ አለኝ የማያስከፍል ፡ ቅጥር ፡ ሆኖኛል ፡ መተማመኛ ማስፈራራቱ ፡ አያገኘኝም ፡ የዛ ፡ ቀማኛ የሚጠብቀኝ ፡ የኔ ፡ አባት አይሰለቸውም ፡ ቀንም ፡ ለሊት የሚጠብቀኝ ፡ የኔ ፡ እረኛ ቀኑን ፡ ጠብቆ ፡ ማታ ፡ ማይተኛ በቀኜ ፡ ነህና ፡ እኔ ፡ አልደነግጥም ሁልግዜ ፡ ስላማህ ፡ አልታወክም ከመከራ ፡ ስጋት ፡ ልቤ ፡ እርፍ ፡ ብሏል ህይወቴ ፡ በእጅህ ፡ ላይ ፡ ነው ፡ ምን ፡ ያስፈራኛል የማያስከፍል ፡ ቅጥር ፡ ሆኖኛል ፡ መተማመኛ ማስፈራራቱ ፡ አያገኘኝም ፡ የዛ ፡ ቀማኛ የሚጠብቀኝ ፡ የኔ ፡ አባት አይሰለቸውም ፡ ቀንም ፡ ለሊት የሚጠብቀኝ ፡ የኔ ፡ እረኛ ቀኑን ፡ ጠብቆ ፡ ማታ ፡ ማይተኛ እኔ ፡ የምኖረው ፡ አንተን ፡ ታምኜ ፡ ነው/2 በህይወት ፡ የምኖረው ፡ ቃልህን ፡ ታምኜ ፡ ነው/2 እግዚአብሔር ፡ እረኛዬ ፡ ነው ሚያሳጣኝ ፡ የለም ፡ የማጣው ፡ የለም/2 እግዚአብሔር ፡ ፀጥታዬ ፡ ነው ሚያውከኝ ፡ የለም/3

ሳምራዊት ሲዛር · ሁሉም ዘማሪዎች