Gubae

Beyemaledaw

ሳምራዊት ሲዛር · Yene Aleme

በየማለዳው ፡ ያንተ ፡ ውለታ ይከተለኝ ፡ በጠላት ፡ እንዳልረታ አይዞሽ ፡ ስትለኝ ፡ ስታስበኝ ከአፌ ፡ መዝሙር ፡ እንዳይጠፋ ፡ አደረከኝ ምን ፡ ልበል ፡ ምን ፡ ላድርግ ፡ ወዶኝ ፡ ነው ፡ ያለልክ/2 ዛሬ ፡ ዛሬስ ፡ ይገርመኛል ሰው ፡ መሆኔ ፡ ይደንወኛል ባለፍኩበት ፡ ጎዳናዬ መከናወኔ ፡ ነው ፡ ጌታዬ አሃሃ ፡ ከፍ ፡ በል ፡ ኦሆሆ ፡ ከፍ ፡ በል/2 አሃሃ ፡ ከፍ ፡ በል ዛሬን ፡ ባንተ ፡ ካለፍኩ ፡ ነገን ፡ ምን ፡ እሆናለው ክንድህ ፡ አስተማማኝ ፡ ተደግፌዋለው ዛሬን ፡ ባንተ ፡ ካለፍኩ ፡ ነገን ፡ ምን ፡ እሆናለው ቃልህ ፡ አስተማማኝ ፡ ተደግፌዋለው ካላጣኸ ፡ ቦታ ፡ ካላጣኸው ፡ ልብ ኧረ ፡ እንዴት ፡ ወደድከኝ ፡ ገረመኝ ፡ ሳስብ ማነው ፡ የወደደኝ ፡ ጠጋ ፡ ያረገኝ ከመሞት ፡ አውጥቶ ፡ ፍቅር ፡ ያሳየኝ ጌታ ፡ ነው/3 ጌታ አንዴ ፡ በቻ ፡ አይደለም ፡ ብዙ ፡ ጊዜ ፡ ነው ፡ ጉልበት ፡ የሆንከኝ እምነቴ ፡ ሲላላ ፡ ከጎኔ ፡ ቀመህ ፡ ያበረታኸኝ መቼም ፡ መቼም ፡ መቼም ፡ ቢሆን ፡ አልረሳውም ፡ ያንተን ፡ ፍቅር ሰው ፡ ያረክኝ ፡ ያወጣኸኝ ፡ ከጨለማው ፡ ከሞት ፡ ገደል/2 በየማለዳው ፡ ያንተ ፡ ውለታ ይከተለኝ ፡ በጠላት ፡ እንዳልረታ አይዞሽ ፡ ስትለኝ ፡ ስታስበኝ ከአፌ ፡ መዝሙር ፡ እንዳይጠፋ ፡ አደረከኝ ምን ፡ ልበል ፡ ምን ፡ ላድርግ ፡ ወዶኝ ፡ ነው ፡ ያለልክ/2 የኔማ ፡ ነገር ፡ የኔ ፡ ጉዳይ ፡ ተፈፀመልኝ ፡ ጎልጎታ ፡ ላይ የኔማ ፡ ነገር ፡ የኔስ ፡ ጉዳይ ፡ ተፈፀመልኝ ፡ ጎልጎታ ፡ ላይ መቼም ፡ መቼም ፡ መቼም ፡ ቢሆን ፡ አልረሳውም ፡ ያንተን ፡ ፍቅር ሰው ፡ ያረክኝ ፡ ያወጣኸኝ ፡ ከጨለማው ፡ ከሞት ፡ ገደል/2

ሳምራዊት ሲዛር · ሁሉም ዘማሪዎች