Gubae

Befeqru Yezognal

ሳምራዊት ሲዛር · እግዚአብሔር መልካም ነህ

ፍቅሩ ፡ ይዞኛል ፡ በደግነቱ ልዘምር ፡ በቃ ፡ ልቁም ፡ በፊቱ (፪x) በፊቴ ፡ የሚቆም ፡ አይኑር ፡ ከልካይ አይሆንልኝም ፡ እሱን (ፊቱን) ፡ ሳላይ (፪x) ቀኑ ፡ አይገፋም ፡ እንዲህ ፡ እንደዋዛ ከኢየሱስ ፡ ውጪ ፡ ምን ፡ አለው ፡ ለዛ (፪x) አዝ፦ ለካስ ፡ ሁሉም ፡ ከንቱ ፡ ነው (እህም) የከንቱ ፡ ከንቱ ፡ ነው አንተን ፡ መያዝ ፡ ግን ፡ ታላቅ ፡ ትርፍ ፡ ነው (፪x) ከጆችህ ፡ አምልጬ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለው ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ኑሮ ፡ ምድረበዳ ፡ ነው (፪x) ከአንተ ፡ ጋር ፡ መኖር ፡ እረፍት ፡ ነው ከአንተ ፡ ጋር ፡ መኖር ፡ ሕይወት ፡ ነው (፪x) አዝንክልኝ ፡ ጌታዪ ፡ እራራህልኝ እጄን ፡ ላንሳ ፡ ልባርክህ ፡ ኦሆሆ ፡ ልባርክህ ልነሳ ፡ ላነሳሳው ፡ እንጂ ፡ ፍቅርህን ፡ ጌታዬ ሳላመልክ ፡ እንዴት ፡ እኖራለው ፡ ማምለክ ፡ ነውና ፡ ድርሻዬ አዝ፦ ለካስ ፡ ሁሉም ፡ ከንቱ ፡ ነው (እህም) የከንቱ ፡ ከንቱ ፡ ነው አንተን ፡ መያዝ ፡ ግን ፡ ታላቅ ፡ ትርፍ ፡ ነው (፪x) ፍቅሩ ፡ ይዞኛል ፡ በደግነቱ ልዘምር ፡ በቃ ፡ ልቁም ፡ በፊቱ (፪x) በፊቴ ፡ የሚቆም ፡ አይኑር ፡ ከልካይ አይሆንልኝም ፡ እሱን (ፊቱን) ፡ ሳላይ (፪x) ቀኑ ፡ አይገፋም ፡ እንዲህ ፡ እንደዋዛ ከኢየሱስ ፡ ውጪ ፡ ምን ፡ አለው ፡ ለዛ (፪x) አዝ፦ ለካስ ፡ ሁሉም ፡ ከንቱ ፡ ነው (እህም) የከንቱ ፡ ከንቱ ፡ ነው አንተን ፡ መያዝ ፡ ግን ፡ ታላቅ ፡ ትርፍ ፡ ነው (፪x)

ሳምራዊት ሲዛር · ሁሉም ዘማሪዎች