Gubae

Yemiyasfelegegnen Yawqal

ነፃነት አሰፋ · አለኝ ብዙ ምስጋና

የሚያስፈልገኝን ፡ እርሱ ፡ ያውቃል  የሰማይ ፡ አባቴ ፡ ለኔ ፡ ያስባል  እጆቼን ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ ዘረጋለሁ  በዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ እታመናለሁ የሚያስጨንቀን ፡ በእርሱ ፡ ጥዬ እታመናለሁኝ ፡ በጌታዬ ጽድቁና ፡ መንግሥቱን ፡ እሻለሁኝ ክብሩን ፡ እያየሁኝ ፡ እጠግባለሁኝ ላመልከው ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ የፈጠረኝ ከእርሱ ፡ ሌላ ፡ ምንም ፡ ላይገዛኝ እያሞጋገስኩኝ ፡ ታላቅ ፡ ስሙን አመልከዋለሁኝ ፡ እግዚአብሔርን የጠራኝ ፡ የለየኝ ፡ የቀደሰኝ ለእርሱ ፡ ካህን ፡ ልሆን ፡ ነው ፡ የቀባኝ እርሱ ፡ ያደረገኝ ፡ እሆናለሁ የኣምላኬን ፡ በጐነት ፡ አወራለሁ መልካሙን ፡ ስራውን ፡ የጀመረው የጠራኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ታማኝ ፡ ነው እስከ ፡ ክርስቶስ ፡ ቀን ፡ ሊፈጽመው ይችላል ፡ አምላኬ ፡ ታማኝ ፡ ነው

ነፃነት አሰፋ · ሁሉም ዘማሪዎች