Gubae

Nefsie Egziabhieren Barki

ነፃነት አሰፋ · እግዚአብሔርን ባርኪ

ነፍሴ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ባርኪ  ነፍሴ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ባርኪ  ሃጥያትሽ ፡ ይቅር ፡ ብሏል ፡ ደዌሽንም ፡ ፈውሷል  ነፍሴ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ባርኪ  ነፍሴ ፡ በምላክሽ ፡ ደስ ፡ ይበልሽ  ነፍሴ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ደስ ፡ ይበልሽ  አምላክሽ ፡ ጠርቶሻልና ፡ ስለአንቺም ፡ ይዋጋልና  ነፍሴ ፡ ባምላክሽ ፡ ደስ ፡ ይበልሽ ከዘመናት ፡ በፊት ፡ ጌታ ፡ አስቦሻል በዘለዓለም ፡ ፍቅሩ ፡ አምላክሽ ፡ ወዶሻል በገዛ ፡ ልጁ ፡ ደም ፡ ራሱ ፡ አቅርቦሻል አሜን ፡ ብይ ፡ ኃጢአትሽ ፡ ተሰርዮሻል የዚህ ፡ ዓለም ፡ ገዢ ፡ ውጊያ ፡ ቢያበዛብሽ መንግድሽን ፡ ሊያጠብ ፡ ዙሪያሽም ፡ ቢዚሮሽ በአምላክሽ ፡ ታመኚ ፡ ስለአንቺ ፡ ይዋጋል የሰራዊት ፡ ጌታ ፡ በፊትሽ ፡ ይሄዳል በልጁ ፡ የዋጀሽ ፡ ጌታሽ ፡ ካንቺ ፡ ጋር ፡ ነው ፡ ኃይለኛው ፡ እግዚአብሔር ፡ አምላክሽ ፡ እርሱ ፡ ነው በድካሙ ፡ ያፈራሽ ፡ ጽድቅሽ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆኗል በወደድሽ ፡ በእርሱ ፡ ምህረት ፡ አግተሻል ስለአንቺ ፡ መስቀል ፡ ላይ ፡ ሁሉን ፡ ተሸክሞአል ስራውን ፡ ጨርሶ ፡ ተፈጽመ ፡ ብሏል ፡ ተንሽ ፡ አመስግኚው ፡ ምህረትሽን ፡ ውሰጂ ለዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ ለኢየሱስ ፡ ስገጂ

ነፃነት አሰፋ · ሁሉም ዘማሪዎች