Gubae

Kante Lemar Eyesus

ነፃነት አሰፋ · ኢየሱስ ፍቅር

ፍቅርን ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ ኢየሱስ ምህረትን ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ ኢየሱስ ፡ ይቅርታን ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ ኢየሱስ ፡ የነፍሴ ፡ ንጉሥ ፡ የሕይወቴ ፡ ንጉሥ  የማይለወጥ ፡ የአንተ ፡ ፍቅር  የማትሰለች ፡ ሁልጊዜ ፡ ምትምር  ይቅርታህ ፡ ብዙ ፡ ከአይምሮ ፡ በላይ  ጌታ ፡ እንተን ፡ አየሁ ፡ በምድር ፡ በሰማይ ትዕግሥትን ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ ኢየሱስ ቸርነት ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ ኢየሱስ ማስተዋል ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ ኢየሱስ የነፍሴ ፡ ንጉሥ ፡ የሕይወቴ ፡ ንጉሥ  አየሁኝ ፡ ጌታ ፡ ስትታገሰኝ  በቸርነትህ ፡ ስትለግሰኝ  ታስደንቃለህ ፡ ማስተዋል ፡ አለህ  ሚመስልህ ፡ የለም ፡ ኢየሱስ ፡ ልዩ ፡ ነህ እውነትን ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ ኢየሱስ ዕውቀትን ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ ኢየሱስ ጥበብን ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ ኢየሱስ የነፍሴ ፡ ንጉሥ ፡ የሕይወቴ ፡ ንጉሥ  አንተ ፡ እውነት ፡ ነህ ፡ እውነተኛ ፡ ነህ  ሁሉን ፡ ፈጥረሃል ፡ ሁሉን ፡ ታውቃለህ  ጥበበኛ ፡ ነህ ፡ የሁሉ ፡ ጌታ  በምንም ፡ ነገር ፡ የማትረታ የዋህነት ፡ ከአንተ ፡ ለማር ፡ ኢየሱስ ትህትናን ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ ኢየሱስ መታዘዝ ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ ኢየሱስ የነፍሴ ፡ ንጉሥ ፡ የሕይወቴ ፡ ንጉሥ  አትጨክንም ፡ አንተ ፡ የዋህ ፡ ነህ  ዝቅ ፡ ማለትን ፡ ታውቅበታለህ  እስከሞት ፡ ድረስ ፡ አንተ ፡ ታዘዝህ  ኢየሱስ ፡ ሙሉ ፡ ነህ ፡ ትማርካለህ

ነፃነት አሰፋ · ሁሉም ዘማሪዎች