Gubae

ጌታ ኢየሱስ

Gieta Eyesus

ነፃነት አሰፋ · እግዚአብሔርን ባርኪ

ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡  የሰማይ ፡ የምድር ፡ ንጉሥ  ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡  የፍጥረታት ፡ ሁሉ ፡ ንጉሥ  ሥሙ ፡ ክብር ፡ አለው  ሥሙ ፡ ክብር ፡ አለው  ሥሙ ፡ ክብር ፡ አለው  ሥሙ ፡ ክብር ፡ አለው ከመጀመሪያው ፡ ያለ ፡ የሁሉ ፡ መሰረት ፡ የሆነ በሰማይም ፡ በምድርም ፡ ሥሙ ፡ እጅግ ፡ የገነነ በእግዚአብሔር ፡ መላዕክቶች ፡ ፊት ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ የከበረ ዙፋኑ ፡ ዘለዓለማዊ ፡ በቅድስናው ፡ ያማረ በእግዚአብሔር ፡ መላዕክቶች ፡ ፊት ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ የከበረ ዙፋኑ ፡ ዘለዓለማዊ ፡ በቅድስናው ፡ ያማረ በወርቅ ፡ መቅረዞች ፡ መሃል ፡ በክብር ፡ ያሚመላለስ ድምጹ ፡ እንደ ፡ ብዙ ፡ ውሃዎች ፡ ድምጽ ፡ እግሮቹ ፡ እንደነጠረ ፡ ናስ ደረቱን ፡ በወርቅ ፡ ታጥቋል ፡ ዓይኖቹ ፡ የእሳት ፡ ነበልባል ከአፉ ፡ ስይፍ ፡ ይወጣል ፡ ፊቱ ፡ አንደ ፡ ፀሐይ ፡ ያበራል ደረቱን ፡ በወርቅ ፡ ታጥቋል ፡ ዓይኖቹ ፡ የእሳት ፡ ነበልባል ከአፉ ፡ ስይፍ ፡ ይወጣል ፡ ፊቱ ፡ አንደ ፡ ፀሐይ ፡ ያበራል መጽሐፊንፉንም ፡ ሊወሰድ ፡ መሐተሞቹን ፡ ሊፈታ ፡ የገባዋል ፡ ኢየሱስ ፡ የጌቴች ፡ ሁሉ ፡ ጌታ ለእግዚአብሔር ፡ አዲስ ፡ ሕዝብን ፡ በደሙ ፡ ስለዋጀ መንግሥትና ፡ ካህናት ፡ ለአምላኩ ፡ አዘጋጀ ለእግዚአብሔር ፡ አዲስ ፡ ሕዝብን ፡ በደሙ ፡ ስለዋጀ መንግሥትና ፡ ካህናት ፡ ለአምላኩ ፡ አዘጋጀ ለወደደን ፡ በደሙ ፡ ከኃጢአታችን ፡ ላጠበን ለአምላኩ ፡ መንግሥትና ፡ ካህናት ፡ ላደረገን በክብር ፡ ለሚመጣው ፡ ኃይል ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን እሰከዘለዓለም ፡ ድረስ ፡ ክብርም ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን በክብር ፡ ለሚመጣው ፡ ኃይል ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን እሰከዘለዓለም ፡ ድረስ ፡ ክብርም ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን

ነፃነት አሰፋ · ሁሉም ዘማሪዎች