Gubae

Endante Yale Amlak

ነፃነት አሰፋ · አለኝ ብዙ ምስጋና

ራስህን ፡ መስዋት ፡ አርገህ ፡ ስለእኛ ፡ ታርደሃል ለአምላክህ ፡ አዲስ ፡ ሕዝብን ፡ በደምህ ፡ ዋጅተሃል መንግሥትና ፡ ካህናት ፡ ለአባትህ ፡ አዘጋጀህ አምልኮ ፡ ውዳሴ ፡ ምሥጋና ፡ ይብዛልህ፡  ፡ ምሥጋና ፡ ይብዛልህ ፡ አምልኮ ፡ ይብዛልህ  ፡ ሌላማ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ለአንተ ፡ የሚሰጥህ  ፡ እንዳተ ፡ ያለ ፡ አዳኝ ፡ አልተገኘምና  ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ይብዛልህ ፡ አምልኮ ፡ ምሥጋና  ፡ ይገባሃልና ከንፈሮችህ ፡ ጠቢብ ፡ በዕውቀት ፡ የላቁ ፡ ጻድቅ ፡ ሆይ ፡ በዕውቀትህ ፡ ብዙዎች ፡ ጸደቁ ለእግዚአብሔር ፡ ማደሪያ ፡ ቤትን ፡ ሰራህለት ፡ አብም ፡ በአንተ ፡ ስራ ፡ ደስ ፡ ተሰኘበት  ፡ ምሥጋና ፡ ይብዛልህ ፡ አምልኮ ፡ ይብዛልህ  ፡ ሌላማ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ለአንተ ፡ የሚሰጥህ  ፡ እንዳተ ፡ ያለ ፡ ጥቢብ ፡ አልተገኘምና  ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ይብዛልህ ፡ አምልኮ ፡ ምሥጋና  ፡ ይገባሃልና ነግስታት ፡ ኃያልን ፡ ጠቢባንም ፡ ጭምር ጌታ ፡ ዝቅ ፡ በለው ፡ ይስጡ ፡ ለአንተ ፡ ክብር ጐልማሶች ፡ ቆንጆዎች ፡ ሽማግሌዎች ፡ ይምጡ ፡ ለታላቅነትህ ፡ ክብርን ፡ ለአንተ ፡ ይስጡ  ፡ ምሥጋና ፡ ይብዛልህ ፡ አምልኮ ፡ ይብዛልህ  ፡ ሌላማ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ለአንተ ፡ የሚሰጥህ  ፡ እንዳተ ፡ ያለ ፡ ጌታ ፡ አልተገኘምና  ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ይብዛልህ ፡ አምልኮ ፡ ምሥጋና  ፡ ይገባሃልና ከመላእክት ፡ በላይ ፡ ከነቢያት ፡ በላይ ከሊቀ ፡ ካህናት ፡ ከአባቶችም ፡ በላይ ተሹመህ ፡ በአብ ፡ ቀኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ተቀምጠሃል አምልኮ ፡ ውዳሴ ፡ ስግደት ፡ ይገባሃል  ፡ ምሥጋና ፡ ይብዛልህ ፡ አምልኮ ፡ ይብዛልህ  ፡ ሌላማ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ለአንተ ፡ የሚሰጥህ  ፡ እንዳተ ፡ ያለ ፡ አምላክ ፡ አልተገኘምና  ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ይብዛልህ ፡ አምልኮ ፡ ምሥጋና  ፡ ይገባሃልና

ነፃነት አሰፋ · ሁሉም ዘማሪዎች