የእኔ ነገር
Yenie Neger
መስከረም ጌቱ · እከተልሃለሁ · 2012
አዝ፦ የእኔን ፡ ነገር ፡ የእኔን ፡ ጉዳይ የያዘልኝ ፡ ጌታ ፡ አለ ፡ ከሰማይ (፪x) ማደሪያው ፡ ልግባና ላምልከው ፡ አንስቼ ፡ በገና (፪x) የማማርረው ፡ አልሞላም ፡ ብዬ ስሙን ፡ ላወድስ ፡ ሀዘኔን ፡ ጥዬ ቢጐድልም ፡ እንኳን ፡ ወይኑ ፡ በለሱ በዚህ ፡ አይለካም ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ እርሱ ጌታ ፡ ነው (፫x) ፡ ጌታ ላመስግነው ፡ ሳለይ ፡ ሁኔታ (፪x) እኔ ፡ አለሁኝ ፡ አለሁኝ ፡ አበዛለው ፡ ብዙ ፡ ምስጋና ሰው ፡ ሆኛለሁ ፡ ጌታዬ ፡ ኢየሱሴ ፡ በሰራው ፡ ስራ ከትላንቱ ፡ ከአስፈሪው ፡ ከጨለማው ፡ ከዚያ ፡ ግዛት ያመለጠ ፡ የዳነ ፡ ለጌታዬ ፡ ይስገድለት አምጡለታ ፡ አምጡለታ ሲያንስበት ፡ ነው ፡ እልልታ ፡ ለዚህ ፡ ጌታ (፪x) አዝ፦ የእኔን ፡ ነገር ፡ የእኔን ፡ ጉዳይ የያዘልኝ ፡ ጌታ ፡ አለ ፡ ከሰማይ (፪x) ማደሪያው ፡ ልግባና ላምልከው ፡ አንስቼ ፡ በገና (፪x) የዘላለም ፡ አባት ፡ የመዳኛ ፡ ደግሞም ፡ ካህኔ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ አምለኬ ፡ የሆነው ፡ ለእኔ ከአባቱ ፡ ቀኝ ፡ ሆኖ ፡ ስለእኔ ፡ እየማለደ ዛሬም ፡ አለው ፡ በእቅፉ ፡ ጠላቴን ፡ እያዋረደ አምጡለታ ፡ አምጡለታ ሲያንስበት ፡ ነው ፡ እልልታ ፡ ለዚህ ፡ ጌታ (፪x) አዝ፦ የእኔን ፡ ነገር ፡ የእኔን ፡ ጉዳይ የያዘልኝ ፡ ጌታ ፡ አለ ፡ ከሰማይ (፪x) ማደሪያው ፡ ልግባና ላምልከው ፡ አንስቼ ፡ በገና (፬x)

