ተመችቶኝ ነው
Temechetogn New
መስከረም ጌቱ · እከተልሃለሁ · 2012
ተመችቶኝ ነው ጌታ ፍቅርህ ተመችቶኝ ነው (፬x) ከአንተ ጋራ መዋል ማደር ከአንተ ጋራ (፬x) ሲከፋኝ ስጨነቅ ሆድ ሲብሰኝ ከጐኔ ሲጠፋ የሚረዳኝ ብቻዬን ያልተውከኝ ምድረ በዳ አለሁኝ የምትል ለተጐዳ አዝ ከአንተ ጋራ መዋል ማደር ከአንተ ጋራ (፬x) ከወረት ያልሆነ ታላቅ ፍቅርህ ሀዘኔን የሚያልፍ መፅናናትህ እምባዬን ያበሰከው ደጋፊዬ ስተክዝ ሆንክልኝ መፅናኛዬ አዝ ከአንተ ጋራ መዋል ማደር ከአንተ ጋራ (፬x) አትከዳኝ አትለወጥ በሁኔታ አተወኝ ስደክም ስበረታ ፍቅርህ የፍቅሮች ሁሉ አውራ ዘለዓለም የሚቀጥል እያበራ አዝ ተመችቶኝ ነው ጌታ ፍቅር ተመችቶኝ ነው (፬x) ከአንተ ጋራ መዋል ማደሩ ከአንተ ጋራ (፪x) ሲከፋኝ ስጨነቅ ሆድ ሲብሰኝ (ከአንተ ጋራ) ከጐኔ ሲጠፋ የሚረዳኝ (ከአንተ ጋራ) ብቻዬን ያልተውከኝ ምድረ በዳ (ከአንተ ጋራ) አለሁኝ የምትል ለተጐዳ (ከአንተ ጋራ) (፪x)

