እየዋለ እያደር
Eyewale Eyader
ለዓለም ጥላሁን · ኃይልንም የሚያስታጥቀኝ · 2000
አዝ:- ሁሉን ፡ አድርገህልኛል ፡ የቀረብኝም ፡ የለም ሌላ ፡ ምልህ ፡ ባይኖረኝ ፡ እወድሃለሁ ፡ እኔም ሌላ ፡ ምልህ ፡ ባይኖረኝ ፡ እወድሃለሁ ፡ እኔም (፪x) የሰማይን ፡ ፀጋ ፡ የምድርን ፡ በረከት በሌላ ፡ እኮ ፡ አይደለም ፡ ባንተ ፡ ነው ፡ ያገኘሁት ጽድቅና ፡ ሰላምን ፡ የመንፈስን ፡ ደስታ አጎናጽፈኅኛል ፡ የሰራዊት ፡ ጌታ (፪x) አዝ:- ሁሉን ፡ አድርገህልኛል ፡ የቀረብኝም ፡ የለም ሌላ ፡ ምልህ ፡ ባይኖረኝ ፡ እወድሃለሁ ፡ እኔም ሌላ ፡ ምልህ ፡ ባይኖረኝ ፡ እወድሃለሁ ፡ እኔም (፪x) ምን ፡ ያጠያይቃል ፡ መልካምነትህ ለኔስ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ በረከቴ ፡ ነህ መወደድ ፡ ስይንስህ ፡ ነው ፡ መች ፡ ይበዛብሃል እንኳን ፡ እኔነቴ ፡ ዘሬ ፡ የገዛልሃል እየዋለ ፡ እያደር ፡ ታምራትህ ፡ በዛ የነገስታት ፡ ንጉስ ፡ የጌቶቹ ፡ ጌታ (፪x) ምን ፡ እንልሃለን ፡ ማዳንህን ፡ እያየን በምስጋና ፡ በላይ ፡ ምስጋናን ፡ እንሰዋለን ምን ፡ እንልሃለን ፡ ምሕረትህን ፡ እያየን በክብርም ፡ በላይ ፡ ክብርን ፡ እንሰጣለን መልካምን ፡ ማድረግ ፡ ማይታክትህ አቤት ፡ እግዚአብሔር ፡ ቸርነትህ ፡ አሃሃ ትላንት ፡ ያረከው ፡ ሳይበቃህ ዛሬም ፡ ደገምከኝ ፡ አብዝተህ (፪x) በክብር ፡ ላይ ፡ ሌላ ፡ ክብር ፡ በክብር ፡ ላይ ፡ አሃ ቆርጫለሁ ፡ ለመጨመር ፡ ከዚያም ፡ በላይ አንደበቴን ፡ በምስጋና ፡ እየከፈትኩ ፡ ኦሆ ለድል ፡ ጌታ ፡ የድል ፡ ዜማን ፡ አመጣለሁ እየዋለ ፡ እያደር ፡ ታምራትህ ፡ በዛ የነገስታት ፡ ንጉስ ፡ የጌቶቹ ፡ ጌታ (፪x) ምን ፡ እንልሃለን ፡ ማዳንህን ፡ እያየን በምስጋና ፡ በላይ ፡ ምስጋናን ፡ እንሰዋለን ምን ፡ እንልሃለን ፡ ምሕረትህን ፡ እያየን በክብርም ፡ በላይ ፡ ክብርን ፡ እንሰጣለን ተራሮችንም ፡ ትክክል ፡ አደረክና ፡ እግዚአብሔር ፡ አሃ የነሃሱን ፡ ደጆች ፡ ሰባብረህ ፡ እኔን ፡ ለክብር ፡ አበቃህ (፪x) በክብር ፡ ላይ ፡ ሌላ ፡ ክብር ፡ በክብር ፡ ላይ ፡ አሃ ቆርጫለሁ ፡ ለመጨመር ፡ ከዚያም ፡ በላይ አንደበቴን ፡ በምስጋና ፡ እየከፈትኩ ፡ ኦሆ ለድል ፡ ጌታ ፡ የድል ፡ ዜማን ፡ አመጣለሁ አምላኬ ፡ መታመኛዬ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ንጉሴ ፡ መደገፊያዬ ፡ ነው ፡ አምባዬ (፪x)

