Gubae

ሁሉም ይስማ

Hulum Yesma

ቄፋ ሚደቅሳ · ሁሉም ይስማ

ዘማሪ ፡ ኬፋ ፡ ሚደቅሳ አልበም ፡ ሁሉም ፡ ይስማ አዝ አንተ ፡ እንደ ፡ ረዳኸኝ አንተ ፡ እንዳነሳኸኝ ሁሉ ፡ ይስማ ፡ ይወቅልኝ ሁሉ ፡ ይስማ ፡ ያመስግንልኝ ሁሉ ፡ ይስማ ፡ ይወቅልኝ ሁሉ ፡ ይስማ ፡ ያመስግንልኝ (፪x) ምደረ ፡ በዳውን ፡ አቋርጫለሁ እጄን ፡ ይዘኸኝ ፡ ኢየሱስ ፡ በሕይወት ፡ ኖሪያለሁ አልነደፈኝም ፡ እባቡ ፡ ጊንጡ አቤት ፡ ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ተረፍኩ ፡ ከስንቱ (፪x) አቤት ፡ አባቴ ፡ በአንተ ፡ ተረፍኩ ፡ ከስንቱ ሲጨላልም ፡ የማይነጋ ፡ ሲመስል የቅርብ ፡ የሩቅ ፡ ገለል ፡ ገለል ፡ ሲል በውድቅቱ ፡ ሌሊቱ ፡ መጣህና በሰልፍ ፡ ቀን ፡ ራሴን ፡ ሸፈንክና አዘመርከኝ (፫x) እንዳዳንኩህ ፡ እንዳገዝኩህ ፡ መስክር ፡ አልከኝ አባት ፡ ሆንከኝ ፡ ክብር ፡ ሆንከኝ ፡ ተሸከምከኝ በደግ ፡ እጅህ ፡ እቅፍ ፡ አርገህ ፡ አነሳኸኝ በምህረትህ ፡ ብዛት ፡ ቤት ፡ አግብተኸኛል ፡ አሃሃ (፪x) ቤት ፡ አግብተኸኛል በፊትህ ፡ ቃል ፡ ደስታ ፡ ለእኔ ፡ ሰጥተኸኛል ፡ አሃሃ (፪x) ለእኔ ፡ ሰጥተኸኛል ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ የማመሰግንህ ፡ ምክኒያቴ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ አሃሃ (፪x) ምክኒያቴ ፡ ብዙ ፡ ነው ከዛ ፡ ከጨካኙ ፡ ነፍሴን ፡ ከሚፈልግ ከአውሬ ፡ አስጥለኸኝ ፡ ነው ፡ አሃሃ (፪x) ከአውሬ ፡ አስጥለኸኝ ፡ ነው አዝ አንተ ፡ እንደ ፡ ረዳኸኝ አንተ ፡ እንዳነሳኸኝ ሁሉ ፡ ይስማ ፡ ይወቅልኝ ሁሉ ፡ ይስማ ፡ ያመስግንልኝ ሁሉ ፡ ይስማ ፡ ይወቅልኝ ሁሉ ፡ ይስማ ፡ ያመስግንልኝ (፪x)

ቄፋ ሚደቅሳ · ሁሉም ዘማሪዎች