Gubae

And Wedaj

ቄፋ ሚደቅሳ · ሁሉ በእጁ ነው

አንድ ፡ ወዳጅ (፪x) ፡ አለኝ ለእኔ ፡ የሞተልኝ (፬x) ቅጣቴን ፡ የተቀጣህልኝ አበሳዬን ፡ ከእኔ ፡ ወሰድክልኝ (፪x) ጌታ ፡ ተባረክልኝ ኢየሱስ ፡ ተባረክልኝ ጌታ ፡ ተባረክልኝ (፪x) ሙግቴን ፡ ተሟግቶ ፡ አሸንፎልኛል ጠላቴ ፡ እንዳይከሰኝ ፡ ነጻ ፡ ነህ ፡ ብሎኛል ይህን ፡ ወዳጄን ፡ ወዳጄ ፡ ነህ ፡ ያልኩት ከማንም ፡ አብልጬ ፡ በልቤ ፡ የሾምኩት አዝ፦ ለእኔ ፡ መልካም ፡ በማድረግ ፡ የታወቀው መልካም ፡ በማድረግ ፡ የታወቀው ለእኔ ፡ መልካም ፡ በማሰብ ፡ የታወቀው መልካም ፡ በማሰብ ፡ የታወቀው እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x) እርሱ ፡ ጌታዬ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ነው (፪x) በምክሩ ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ ነፍስን ፡ ይመልሳል ከወዳጅ ፡ አብልጦ ፡ ወደ ፡ ልብ ፡ ይጠጋል ደብቆ ፡ የያዘኝ ፡ እንዳልሆን ፡ የሌላ የቅርቤ ፡ የምለው ፡ ማነው ፡ ከእርሱ ፡ ሌላ አዝ፦ ለእኔ ፡ መልካም ፡ በማድረግ ፡ የታወቀው መልካም ፡ በማድረግ ፡ የታወቀው ለእኔ ፡ መልካም ፡ በማሰብ ፡ የታወቀው መልካም ፡ በማሰብ ፡ የታወቀው እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x) እርሱ ፡ ጌታዬ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ነው (፪x)

ቄፋ ሚደቅሳ · ሁሉም ዘማሪዎች