Gubae

Lenesa Lamesgin

ካሳሁን ለማ · እግዚአብሔር ቀን አለው

በቃልህ ፡ ትእዛዝ ፡ በስልጣንህ ፡ በትር ሁሉን ፡ ትገዛለህ ፡ ላንተ ፡ ይሁን ፡ ክብር ከክብር ፡ ጋር ፡ ስፍራን ፡ በቀኝህ ፡ ሰጠኸኝ ምን ፡ ቢለፋ ፡ ቢጥር ፡ ጠላቴ ፡ አያገኘኝ አዝ፦ ልነሳ ፡ ላመስግን ፡ ዝቅ ፡ ዝቅ ፡ ብዬ ፡ ከእግርህ ፡ ስር ልሰዋ ፡ ምስጋና ፡ ክብር ፡ የሚገባህ ፡ ነህና (፪x) ክብር ፡ የሚገባህ ፡ ነህና (፬x) በሚታየው ፡ አልለውጥህም በሁኔታ ፡ አልገምትህም ቢመሽም ፡ ቢነጋም ፡ አውቃለሁ አንተን ፡ ለማመስገን ፡ እቆማለሁ ፡ ፪x አዝ፦ ልነሳ ፡ ላመስግን ፡ ዝቅ ፡ ዝቅ ፡ ብዬ ፡ ከእግርህ ፡ ስር ልሰዋ ፡ ምስጋና ፡ ክብር ፡ የሚገባህ ፡ ነህና (፪x) ክብር ፡ የሚገባህ ፡ ነህና (፬x) ዘመኔን ፡ በክብርህ ፡ አስዋብከው ፡ ከአውሬና ፡ ከተኩላው ፡ አድነህ ከክብር ፡ ወደ ፡ ክብር ፡ መራኸኝ ፡ በእጅህ ፡ እጄን ፡ ይዘህ ታሪኬ ፡ ሆንክልኝ ፡ ትምክቴ ፡ ትርጉም ፡ ለሕይወቴ አመሰግናለሁ ፡ ከፍ ፡ በል ፡ ኢየሱስ ፡ መድኃኒቴ (፪x) አዝ፦ ልነሳ ፡ ላመስግን ፡ ዝቅ ፡ ዝቅ ፡ ብዬ ፡ ከእግርህ ፡ ስር ልሰዋ ፡ ምስጋና ፡ ክብር ፡ የሚገባህ ፡ ነህና (፪x) ክብር ፡ የሚገባህ ፡ ነህና (፬x) እንደ ፡ ባለማዕረግ ፡ ተቀብለኸኛል እቅፍህ ፡ ይደላል ፡ ተመችተኸኛል የሕይወቴ ፡ እርካታ ፡ አንተ ፡ ከሆንክልኝ ዓይኔ ፡ ሌላ ፡ አያይም ፡ ምን ፡ ሊፈይድልኝ (፪x) አዝ፦ ልነሳ ፡ ላመስግን ፡ ዝቅ ፡ ዝቅ ፡ ብዬ ፡ ከእግርህ ፡ ስር ልሰዋ ፡ ምስጋና ፡ ክብር ፡ የሚገባህ ፡ ነህና (፪x) ክብር ፡ የሚገባህ ፡ ነህና (፬x)

ካሳሁን ለማ · ሁሉም ዘማሪዎች