Gubae

Keliku Ayalfim

ካሳሁን ለማ · እግዚአብሔር ቀን አለው

"ወይ ፡ የምታልፍ ፡ ብሎ ፡ ያለወትሮው ፡ ሞልቶ ፡ ዮርዳኖስ ፡ ቢፎክር ፡ ቢቆምም ፡ ከፊቴ በዳር ፡ አስከ ፡ ክብር ፡ እሄዳለሁ ፡ አልፈራም ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ጉልበቴ ረግጬው ፡ አልፋለሁ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ጉልበቴ ፣ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ጉልበቴ" አዝ፦ ቢጮህም ፡ አያሸንፍም ፡ ቢጎርፍም ፡ ከልኩ ፡ አያልፍም የጠራኝ ፡ ከኔ ፡ ጋራ ፡ ነው ፡ ለጠላት ፡ ዕድል ፡ አልሰጠው (፪x) ለጠላት ፡ ዕድል ፡ አልሰጠው (፬x)   ሰባት ፡ እጥፍ ፡ ብያነድ ፡ ጠላቴ ፡ እሳቱን ፡ አብዝቶ ከከፍታዬ ፡ ላይ ፡ አልወርድም ፡ ስፍራ ፡ አለቅም ፡ ከቶ የመቆሜ ፡ ሚስጥር ፡ ጌታ ፡ እንጂ ፡ አይደለም ፡ ሁኔታ የታመንኩበትን ፡ አውቃለሁ ፡ አንደማይረታ (፪x)   አዝ፦ ቢጮህም ፡ አያሸንፍም ፡ ቢጎርፍም ፡ ከልኩ ፡ አያልፍም የጠራኝ ፡ ከኔ ፡ ጋራ ፡ ነው ፡ ለጠላት ፡ ዕድል ፡ አልሰጠው (፪x) ለጠላት ፡ ዕድል ፡ አልሰጠው (፬x) ጠላቴን ፡ ከፊቴ ፡ አውጥቶት ፡ አጥፋው ፡ ብሎ ፡ አዞኛል አስጨናቂውን ፡ ዘንግ ፡ ጌታ ፡ ፈጥኖ ፡ ሰብሮልኛል የከፍተኛነቴ ፡ ሰይፍ ፡ ብቃቴም ፡ እርሱ ፡ ነው አትፍራ ፡ ሰላለኝ ፡ አልፈራም ፡ ጌታ ፡ ከኔ ፡ ጋር ፡ ነው (፪x) ጌታ ፡ ከኔ ፡ ጋር ፡ ነው(፬x) አዝ፦ ቢጮህም ፡ አያሸንፍም ፡ ቢጎርፍም ፡ ከልኩ ፡ አያልፍም የጠራኝ ፡ ከኔ ፡ ጋራ ፡ ነው ፡ ለጠላት ፡ ዕድል ፡ አልሰጠው (፪x) ለጠላት ፡ ዕድል ፡ አልሰጠው (፬x)   ከትላንቱ ፡ ይልቅ ፡ ዛሬ ፡ አስደንቆኛል (፪x) እግዚአብሔር ፡ ስራዬን ፡ ሁሉ ፡ ሰርቶልናል (፪x) ላመስግነው ፡ አንጂ ፡ ስሙን ፡ በዝማሬ (፪x) ለጠላቴ ፡ ሃዘን ፡ የድል ፡ ቀን ፡ ነው ፡ ዛሬ ፣ የድል ፡ ቀን ፡ ነው ፡ ዛሬ (፪x) አዝ፦ ቢጮህም ፡ አያሸንፍም ፡ ቢጎርፍም ፡ ከልኩ ፡ አያልፍም የጠራኝ ፡ ከኔ ፡ ጋራ ፡ ነው ፡ ለጠላት ፡ ዕድል ፡ አልሰጠው (፪x) ለጠላት ፡ ዕድል ፡ አልሰጠው (፱x)

ካሳሁን ለማ · ሁሉም ዘማሪዎች