Eyesus Yehiwotie
ካሳሁን ለማ · እግዚአብሔር ቀን አለው
በእቅፍህ ፡ መሃል ፡ ስፍራን ፡ ሰጠኸኝ ፡ ተደላድዬ እፎይ ፡ ብያለሁ ፡ አንተን ፡ አግኝቼ ፡ ክበር ፡ ጌታዬ እንዳልታወክ ፡ በቀኜ ፡ አለህ ፡ ውስጤ ፡ መች ፡ ሰግቶ ልቤም ፡ ይጣራል ፡ ኢየሱስ ፡ እያለ ፡ በፍቅርህ ፡ ነዶ (፪x) አዝ፦ (ኢየሱስ) ፡ የሕይወቴ ፡ ትርጉም ፡ (ኢየሱስ) ፡ የሆንክልኝ ፡ ፍቺ (፪x) (ኢየሱስ) ፡ ክብርን ፡ አይቻለሁ ፡ (ኢየሱስ) ፡ እኔስ ፡ በአንተ ፡ እጅ (፪x) ሁሉን ፡ ቻይ ፡ አምላክ ፡ ወረት ፡ የማታውቅ ፡ እሩህሩህ ፡ ጌታ ፍቅርህ ፡ ማረከኝ ፡ የአንተ ፡ እንድሆን ፡ ልቤም ፡ ተረታ ሌላ ፡ አይገዛንም ፡ ከአንተ ፡ በስተቀር ፡ በምድር ፡ ያለው ሁሉ ፡ የሞላህ ፡ ባለ ፡ ፀጋ ፡ አምላክ ፡ አንተን ፡ ይዣለሁ (፪x) ክበርልኝ (፫x) አላየሁም ፡ ከአንተ ፡ የሚበልጥብኝ ንገስልኝ (፫x) አልሰማሁም ፡ ከአንተ ፡ የሚበልጥብኝ አላየሁም ፡ ከአንተ ፡ የምበልጥብኝ አልሰማሁም ፡ ከአንተ ፡ የምበልጥብኝ (፪x) ስትሾም ፡ ስትሸልም ፡ (አቤት ፡ ስታውቅበት) ደርሰህ ፡ ብርሃን ፡ (ስትሆን ፡ ቀን ፡ ለጨለመበት) ስታውቅበት ፡ ማበጃጀት

