Gubae

እግዚአብሔር ቀን አለው

Egziabhier Qen Alew

ካሳሁን ለማ · እግዚአብሔር ቀን አለው

ርዕስ እግዚአብሔር ቀን አለው ዘማሪ ካሳሁን ለማ አልበም እግዚአብሔር ቀን አለው ለቅሶ ማታ ቢሆንም ጠዋት ደስታp ይሆናል ሁሉን ቻዩ ጌታ እግዚአብሔር ቀን ያዛል (፪x) አዝ ቢመሽም ይነጋል ይነጋል ይህንን አውቃለሁ እንደጨለመ አይቀር አይቀርም እግዚአብሔር ቀን አለው (፪x) እግዚአብሔር ቀን አለው ለሁሉ እግዚአብሔር ቀን አለው (፪x) አልገፋ ብሉ ትላንት ያስቸገረኝ ከፊቴ እየቆመ አላሳልፍ ያለኝ ታሪክን በታሪክ በሚሽረው ጌታ ሁሉ ተለወጠ በቃ ሲል አበቃ (፪x) አያሳፍር ለተደገፉበት ይታመናል ተስፋ ላረጉበት መልካም አምላክ ሁሌም ባለፀጋ እንደርሱ የለም ፈጥኖ የሚረዳ (፪x) አዝ ቢመሽም ይነጋል ይነጋል ይህንን አውቃለሁ እንደጨለመ አይቀር አይቀርም እግዚአብሔር ቀን አለው (፪x) እግዚአብሔር ቀን አለው ለሁሉ እግዚአብሔር ቀን አለው (፪x) አንድ ጊዜ ቃሉን ሲሰጥ ሊሰራ ሲነሳ ነገር ሁሉ ይለወጣል ከእርሱ የተነሳ እኔም ይሄ ገብቶኝ ተደግፌዋለሁ በኃያላን መሃል ኃይል የእግዚአብሄር ነው በኃያላን መሃል ኃይል የእግዚአብሄር ነው (፪x) ኃይል የእግዚአብሔር ነው (፰x) ለቅሶ ማታ ቢሆንም ጠዋት ደስታ ይሆናል ሁሉን ቻዩ ጌታ እግዚአብሔር ቀን ያዛል (፪x) አዝ ቢመሽም ይነጋል ይነጋል ይህንን አውቃለሁ እንደጨለመ አይቀር አይቀርም እግዚአብሔር ቀን አለው (፪x) እግዚአብሔር ቀን አለው ለሁሉ (እግዚአብሔር) እግዚአብሔር ቀን አለው (፬x)

ካሳሁን ለማ · ሁሉም ዘማሪዎች