Ante Tamagn Neh
ካሳሁን ለማ · እግዚአብሔር ቀን አለው
ማለዳ ፡ ማለዳ ፡ ምህረትህ ፡ አዲስ ፡ ነው ታማኝነትህም ፡ እጅጉን ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x) ማለዳ ፡ ማለዳ ፡ ምህረትህ ፡ አዲስ ፡ ነው ታማኝነትህም ፡ እጅጉን ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x) አዝ፦ ታማኝ ፡ ነህ ፡ ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ ነህ (፬x) ጉልበት ፡ ሲዝል ፡ አቅም ፡ ጠፍቶ ፡ አይዞህ ፡ ባይ ፡ ሲታጣ ማን ፡ እንዳንተ ፡ የኔ ፡ ጌታ ፡ አለሁ ፡ ባይ ፡ መከታ ቢደገፉት ፡ እሚያኮራ ፡ ቢታመኑት ፡ ታማኝ አይገኝም ፡ ካንተ ፡ በቀር ፡ በምድርም ፡ በሰማይ አዝ፦ ታማኝ ፡ ነህ ፡ ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ ነህ (፬x) ጠላት ፡ ቢዋዥ ፡ በኃይልህ ፡ ላይ ፡ ትርፉ ፡ ድካሙ ፡ ነው ያልከው ፡ አይቀር ፡ ይፈጸማል ፡ ምክርህ ፡ የጸና ፡ ነው ትላንትናን ፡ እንደሰራህ ፡ ዛሬም ፡ ትሰራለህ ፡ ክንድህ ፡ አይዝል ፡ አስተማማኝ ፡ ሁልጊዜም ፡ ታማኝ ፡ ነህ አዝ፦ ታማኝ ፡ ነህ ፡ ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ ነህ (፬x) አንተን ፡ ይዞ ፡ ማን ፡ አፈረ ፡ ካንተ ፡ የተጠጋ አድነኸው ፡ አማረበት ፡ ከጠላት ፡ መንጋጋ ታሪክ ፡ መስራት ፡ ልማድህ ፡ ነው ፡ ክንድህ ፡ አይታክትም እርስትህን ፡ አሳልፈህ ፡ ለጠላት ፡ አትሰጥም አዝ፦ ታማኝ ፡ ነህ ፡ ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ ነህ (፬x) ማለዳ ፡ ማለዳ ፡ ምህረትህ ፡ አዲስ ፡ ነው ታማኝነትህም ፡ እጅጉን ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x) አዝ፦ ታማኝ ፡ ነህ ፡ ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ ነህ (፬x) በዙሪያዬ ፡ ጋሻ ፡ የእሳት ፡ ቅጥር ፡ ሆነ ከጥፋት ፡ ማምለጫ ፡ ኢየሱስ ፡ አለቴ ፡ ነህ በለመለመ ፡ መስክ ፡ መምራት ፡ ስታውቅበት የዘላለም ፡ ብርሃን ፡ ቀን ፡ ለጨለመበት የዘላለም ፡ ብርሃን ፡ ነህ ፡ የዘላለም ፡ ብርሃን (፰x) ማለዳ ፡ ማለዳ ፡ ምህረትህ ፡ አዲስ ፡ ነው ታማኝነትህም ፡ እጅጉን ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x) ማለዳ ፡ ማለዳ ፡ ምህረትህ ፡ አዲስ ፡ ነው ታማኝነትህም ፡ እጅጉን ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x) አዝ፦ ታማኝ ፡ ነህ ፡ ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ ነህ (፬x) ጉልበት ፡ ሲዝል ፡ አቅም ፡ ጠፍቶ ፡ አይዞህ ፡ ባይ ፡ ሲታጣ ማን ፡ እንዳንተ ፡ የኔ ፡ ጌታ ፡ አለሁ ፡ ባይ ፡ መከታ ቢደገፉት ፡ እሚያኮራ ፡ ቢታመኑት ፡ ታማኝ አይገኝም ፡ ካንተ ፡ በቀር ፡ በምድርም ፡ በሰማይ አዝ፦ ታማኝ ፡ ነህ ፡ ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ ነህ (፬x) ጠላት ፡ ቢዋዥ ፡ በኃይልህ ፡ ላይ ፡ ትርፉ ፡ ድካሙ ፡ ነው ያልከው ፡ አይቀር ፡ ይፈጸማል ፡ ምክርህ ፡ የጸና ፡ ነው ትላንትናን ፡ እንደሰራህ ፡ ዛሬም ፡ ትሰራለህ ፡ ክንድህ ፡ አይዝል ፡ አስተማማኝ ፡ ሁልጊዜም ፡ ታማኝ ፡ ነህ አዝ፦ ታማኝ ፡ ነህ ፡ ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ ነህ (፬x) አንተን ፡ ይዞ ፡ ማን ፡ አፈረ ፡ ካንተ ፡ የተጠጋ አድነኸው ፡ አማረበት ፡ ከጠላት ፡ መንጋጋ ታሪክ ፡ መስራት ፡ ልማድህ ፡ ነው ፡ ክንድህ ፡ አይታክትም እርስትህን ፡ አሳልፈህ ፡ ለጠላት ፡ አትሰጥም አዝ፦ ታማኝ ፡ ነህ ፡ ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ ነህ (፬x) ማለዳ ፡ ማለዳ ፡ ምህረትህ ፡ አዲስ ፡ ነው ታማኝነትህም ፡ እጅጉን ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x) አዝ፦ ታማኝ ፡ ነህ ፡ ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ ነህ (፬x) በዙሪያዬ ፡ ጋሻ ፡ የእሳት ፡ ቅጥር ፡ ሆነ ከጥፋት ፡ ማምለጫ ፡ ኢየሱስ ፡ አለቴ ፡ ነህ በለመለመ ፡ መስክ ፡ መምራት ፡ ስታውቅበት የዘላለም ፡ ብርሃን ፡ ቀን ፡ ለጨለመበት የዘላለም ፡ ብርሃን ፡ ነህ ፡ የዘላለም ፡ ብርሃን (፰x)

