Gubae

ያለምህረትህ ምን አለኝ

Yalemehereteh

ቃልኪዳን ጥላሁን · በየት ሀገር ነው እግዚአብሔር

ዘማሪ ፡ ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን ሌላ ፡ ሥም ፡ ሊሊ ርዕስ ፡ ያለምህረትህ ፡ ምን ፡ አለኝ ያለምህረትህ ፡ ምን ፡ አለኝ ያለ ፡ ይቅርታህ ፡ ምን ፡ አለኝ ምን ፡ አለኝ ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ (፬x) ያለምህረትህ ፡ ምን ፡ አለኝ ያለ ፡ ይቅርታህ ፡ ምን ፡ አለኝ ምን ፡ አለኝ ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ(፮x) የምህረት ፡ ደጆችህ ፡ ተከፍተውልኛል እጅህም ፡ ለእኔ ፡ ተዘርግቶልኛል (፪x) እመጣለሁ ፡ ወደ ፡ አንተ እገባለሁ ፡ የእኔ ፡ ጌታ እገባለሁ ፡ እገባለሁ ፡ የእኔ ፡ ጌታ እመጣለሁ ፡ ወደ ፡ አንተ እመጣለሁ ፡ የእኔ ፡ ጌታ እመጣለሁ ፡ እመጣለሁ ያለምህረትህ ፡ ምን ፡ አለኝ ያለ ፡ ይቅርታህ ፡ ምን ፡ አለኝ ምን ፡ አለኝ ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ (፬x) የእኔ ፡ መታመኛ ፡ ምህረትህ ፡ ብቻ ፡ ነው ድፍረት ፡ የሚሰጠኝ ፡ የፍቅር ፡ ፊትህ ፡ ነው (፪x) እመጣለሁ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ እመጣለሁ ፡ የእኔ ፡ ጌታ እገባለሁ ፡ እገባለሁ ፡ ወደ ፡ አንተ እመጣለሁ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ እመጣለሁ ፡ ወደ ፡ አንተ እመጣለሁ ፡ እመጣለሁ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ተባረክ ፡ ጌታ ፡ ተባረክ ተባረክ ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ ተባረክ ፡ ጌታ ፡ ተባረክ ተባረክ ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ (፪x) ኢየሱስ ፡ መባና ፡ መሰዋእት ኢየሱስ ፡ የመዓዛ ፡ ሽታ ኢየሱስ ፡ አድርጐ ፡ እራሱን ኢየሱስ ፡ የሰጠኝ ፡ ጌታ ኢየሱስ ፡ እኔ ፡ አመልከዋለሁ ኢየሱስ ፡ ቀንም ፡ ሆነ ፡ ማታ የርህራሄ ፡ አባት ፡ የመጽናናት ፡ ሁሉ ፡ አምላክ የሆነ ፡ ጌታችን ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ አምላክና ፡ አባት ፡ ይባረክ የርህራሄ ፡ አባት ፡ የመጽናናት ፡ ሁሉ ፡ አምላክ የሆነ ፡ ጌታችን ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ አባትና ፡ አምላክ ፡ ይባረክ ተባረክ ፡ ጌታ ፡ ተባረክ ተባረክ ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ (፭x)

ቃልኪዳን ጥላሁን · ሁሉም ዘማሪዎች