ውሃ ውሃ እንዳይል
Weha Weha Endayel
ቃልኪዳን ጥላሁን · ለእግዚአብሔር ቀላል ነው
ዘማሪ ፡ ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን አልበም ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ቀላል ፡ ነው ርዕስ ፡ ውኃ ፡ ውኃ ፡ እንዳይል ውኃ ፡ ውኃ ፡ እንዳይል ፡ ሕይወቴን ፡ አጣፍጠህ ይሄ ፡ ነው ፡ የማይባል ፡ ልዩ ፡ ጣዕም ፡ ሰጥተህ (2) መኖር ፡ አስመኘኸኝ ፡ መኖር ፡ መኖር ፡ አለኝ መኖር ፡ የሚያስወድድ ፡ ኢየሱስ ፡ ስላለኝ ውኃ ፡ ውኃ ፡ እንዳይል ፡ ሕይወቴን ፡ አጣፍጠህ ይሄ ፡ ነው ፡ የማይባል ፡ ልዩ ፡ ጣዕም ሰጥተህ (፪x) መኖር ፡ አስመኘኸኝ ፡ መኖር ፡ መኖር ፡ አለኝ መኖር ፡ የሚያስወድድ ፡ ኢየሱስ ፡ ስላለኝ (፪x) እንደገና ፡ አመልክሃለሁ (፫X) እንደገና ፡ አከብርሃለሁ (፫X) ይበቃኝ ፡ ነበረ ፡ እስካሁን ፡ የባረከኝ አንተ ፡ አልበቃህም ፡ ዎይ ባርከኸኝ ፡ ባርከኸኝ (፪x) ይበቃኝ ፡ ነበረ ፡ ራስህን ፡ የሰጠኸኝ አንተ ፡ አልበቃህም ፡ ዎይ ፡ ሰጠኸኝ ፡ ሰጠኸኝ (፪x) እንደገና ፡ አመልክሃለሁ ፡ እንደገና ፡ አሃአሃ እንደገና ፡ እሰጥሃለሁ ፡ እንደገና አሃአሃ ገነት ፡ ገብቻለሁ ፡ እዚሁ ፡ ምድር ፡ ላይ አልጠብቅም ፡ ገና ፡ እስክሄድ ፡ ሠማይ ፡ ላይ (፪x) ገነቴ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ እዚሁ ፡ ምድር ፡ ላይ እኔ ፡ አልጠብቅም ፡ ገና ፡ እስክሄድ ፡ ሠማይ ፡ ላይ (፪x) እንደገና ፡ አመልክሃለሁ ፡ እንደገና ፡ አሃአሃ እንደገና ፡ አከብርሃለሁ ፡ እንደገና ፡ አሃአሃ አልጠገብኩምና ፡ አልረካሁምና እኔ ፡ አመልክሃለሁ ፡ ዛሬም ፡ እንደገና አልጠገብኩምና ፡ አልረካሁምና አመሰግናለሁ ፡ ዛሬም ፡ እንደገና እንደገና ፡ አመልክሃለሁ ፡ እንደገና ፡ አሃአሃ እንደገና ፡ አሃአሃ እንደገና ፡ አከብርሃለሁ ፡ እንደገና ፡ አሃአሃ እንደገና ፡ አሃአሃ (፪x)

