ነፍሴን በፊትህ
Nefsen Befiteh
ቃልኪዳን ጥላሁን · ጨለማዬን ጌታ እያበራ
ነፍሴን በፊትህ አፈሣለው ይኸው 2× ጌታ ምሥጋናዬን ዝም አትበለው ተቀበለው ይኸው 2× ስምህ በእኔ ላይ ተጠርቷልና የመጥራቱ ተስፋ ገብቶኛልና ልሣኔ ባንተ ሃሴት አረገ ልቤም ሁል ጊዜ አንተን ፈለገ ነፍሴን በፊትህ አፈሣለው ይኸው 2× ጌታ ምሥጋናዬን ዝም አትበለው ተቀበለው ይኸው ያከበሩህን ታከብራለህ የሚወዱህን ትወዳለህ ተግተው ለሚሹህ ትገኛለህ እግዚአብሔር አምላክ እንደቃልህ እራሴን ከእግርህ በታች አዋርዳለው /3× በጊዜው ከፍ የሚያደርግ እንዳንተ ማነው /3× ያከበሩህን ታከብራለህ የሚወዱህን ትወዳለህ ተግተው ለሚሹህ ትገኛለህ እግዚአብሔር አምላክ እንደቃልህ

