ማነው
Manew
ቃልኪዳን ጥላሁን · እዩልኝ
እስትንፋስ ፡ ያላቸው ፡ ፍጥረታት ፡ በሙሉ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ ይላሉ አንዳንዱ ፡ ፈልጎ ፡ አንዳንዱ ፡ በግድ አያስደንቅ ፡ ወይ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ሲሰግድን ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው?4x እንዳንተ ፡ ማነው?4x አህዛብ ፡ ደንግጡ ፡ ምድርን ፡ ተፍራው ፈላጭ ፡ ቆራጩ እሱ ፡ ብቻ ፡ ነው ታፍሮና ፡ ተከብሮት ፡ በዙፋኑ ፡ ያለው ከእግዚአብሔር ፡ በስተቀር ፡ የትኛው ፡ አምላክ ፡ ነው? ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው?4x እንዳንተ ፡ ማነው?4x የእድሜ ፡ ባለ ፡ ጸጋ ፡ ሁሌ ፡ አንፀባራቂ ለሰማይ ፡ ለምድሩ ፡ ለፍጥረቱ ፡ በቂ ከዘላለም ፡ በፊት ፡ ከጥንት ፡ የነበረው እግዚአብሔርን ፡ በዕድሜ ፡ የሚበልጠው ፡ ማነው ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው?4x እንዳንተ ፡ ማነው?4x የነገስታትን ፡ ወገብ ፡ የሚፈታ ፡ የሚፈታ ፡ ያኔ ፡ ጌታ ብቻውን ፡ ብዙ ፡ ገጥሞ ፡ የሚረዳ ፡ የኔ ፡ ጌታ ቃላቶች ፡ ተጨምቀው ፡ አንድ ፡ ቃል ፡ ቢሆኑም ያንተን ፡ ትልቅነት ፡ ሊገልፁት ፡ አይችሉም ማነው ፡ የላቀ ፡ የደመቀ ፡ በዓለም ፡ የታወቀ ማነው ፡ ያወቀ ፡ የረቀቀ ፡ ሁሌ ፡ የተደነቀ ማነው ፡ የጸና ፡ ያልወደቀ ፡ ሁሌ ፡ እንደደመቀ በትረ ፡ መንግስቱን ፡ ያለቀቀ ፡ ዘመኑ ፡ ያላለቀ እናገራለሁኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ብዬ እመሰክራለሁ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ብዬ በግምት ፡ አይደለም ፡ የምናገረው ሁሉን ፡ ቻይነቱን ፡ ስለማውቀው ፡ ነው በመላ ፡ እኮ ፡ አይደለም ፡ የምናገረው ሁሉን ፡ ቻይነቱን ፡ ስለማውቀው ፡ ነው ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው?4x እንዳንተ ፡ ማነው?4x

