Kitir Serteh
ቃልኪዳን ጥላሁን · ጨለማዬን ጌታ እያበራ
አዝ፦ ቅጥር ፡ ሰርተህ ፡ እኔን ፡ ከበህ እንደ ፡ ዓይንህ ፡ ብሌን ፡ ተጠንቅቀህ አቤት ፡ ጥበቃህ ፡ ጥበቃህ ፡ ያስደንቀኛል ከክፉ ፡ ሁሉ ፡ ሁሉ ፡ አድነኸኛል (፪x) እግዚአብሔር ፡ መሪ ፡ ነው ፡ ሁሌ ፡ ይመራኛል ከረግረግ ፡ ከጭቃ ፡ እኔን ፡ ያወጣኛል እግሬን ፡ በሰላሙ ፡ መንገድ ፡ የሚያቀና የታመነ ፡ አምላክ ፡ ይድረሰው ፡ ምሥጋና አዝ፦ ቅጥር ፡ ሰርተህ ፡ እኔን ፡ ከበህ እንደ ፡ ዓይንህ ፡ ብሌን ፡ ተጠንቅቀህ አቤት ፡ ጥበቃህ ፡ ጥበቃህ ፡ ያስደንቀኛል ከክፉ ፡ ሁሉ ፡ ሁሉ ፡ አድነኸኛል እግዚአብሔር ፡ መንፈስ ፡ ወደ ፡ እውነት ፡ መርቶኛል በትዕዛዛትህ ፡ እንድሄድ ፡ አድርጐኛል የቅዱሳንህን ፡ እግር ፡ የምትጠብቅ በክንፎችህ ፡ ጥላ ፡ እኔን ፡ የምትደብቅ አዝ፦ ቅጥር ፡ ሰርተህ ፡ እኔን ፡ ከበህ እንደ ፡ ዓይንህ ፡ ብሌን ፡ ተጠንቅቀህ አቤት ፡ ጥበቃህ ፡ ጥበቃህ ፡ ያስደንቀኛል ከክፉ ፡ ሁሉ ፡ ሁሉ ፡ አድነኸኛል እርሱ ፡ የወደደው ፡ ተማምኖ ፡ ይኖራል በትከሻው ፡ መሃል ፡ በክብርም ፡ ያድራል እኔም ፡ ተወደድኩኝ ፡ ፍቅሩንም ፡ አየሁኝ እግዚአብሔር ፡ ሳሳልኝ ፡ ተጠነቀቀልኝ አዝ፦ ቅጥር ፡ ሰርተህ ፡ እኔን ፡ ከበህ እንደ ፡ ዓይንህ ፡ ብሌን ፡ ተጠንቅቀህ አቤት ፡ ጥበቃህ ፡ ጥበቃህ ፡ ያስደንቀኛል ከክፉ ፡ ሁሉ ፡ ሁሉ ፡ አድነኸኛል (፬x)

