Gubae

እጅግ የሚመር

Ejeg Yemimer

ቃልኪዳን ጥላሁን · በየት ሀገር ነው እግዚአብሔር

ዘማሪ ፡ ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን ሌላ ፡ ሥም ፡ ሊሊ ርዕስ ፡ እጅግ ፡ የሚምር አልበም ፡ በየት ፡ ሃገር ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ጻድቅ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ ስራህ ፡ ትክክል የማታደላ ፡ የማትበድል ለታላቅነትህ ፡ ፍጻሜ ፡ የለው አቤት ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ስራህ ፡ ድንቅ ፡ ነው ምላሴ ፡ ጽድቅህን ፡ ሁልጊዜ ፡ ምሥጋናህን ፡ ይናገራል (፫x) ምላሴ ፡ ጽድቅህን ፡ ሁልጊዜ ፡ ምሥጋናህን ፡ ይናገራል (፫x) ደግሜ ፡ ደጋግሜ ፡ እባርክሃለሁ ምሥጋና ፡ ዘወትር ፡ ዘወትር ፡ በአፌ ፡ ነው ማለዳ ፡ በምሥጋና ፡ አፌን ፡ እከፍታለሁ ከአንደበቴ ፡ ፍሬ ፡ ለአንተው ፡ እነግራለሁ ምላሴ ፡ ጽድቅህን ፡ ሁልጊዜ ፡ ምሥጋናህን ፡ ይናገራል (፫x) ምላሴ ፡ ጽድቅህን ፡ ሁልጊዜ ፡ ምሥጋናህን ፡ ይናገራል (፫x) አዝ እጅግ ፡ የሚምር ፡ የሚራራ አምላክ ፡ ነውና ፡ የእኔ ፡ ጌታ ይድረሰው ፡ ምሥጋና ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ይድረሰው ፡ ምሥጋና (፪x) እንኳንስ ፡ ምረሄኝ ፡ ቀርቶልኝ ፡ አበሳ (፪x) እኔስ ፡ ምሥጋናዬን ፡ ሁልጊዜው ፡ አልረሳ (፪x) ምህረትህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ጠንክራለችና (፪x) ኃይሌ ፡ ታድሶልኝ ፡ ቆምኩኝ ፡ እንደገና (፪x) አዝ እጅግ ፡ የሚምር ፡ የሚራራ አምላክ ፡ ነውና ፡ የእኔ ፡ ጌታ ይድረሰው ፡ ምሥጋና ፡ የእኔ ፡ ጌታ ይድረሰው ፡ ምሥጋና የእኔ ፡ ጌታ ፡ ይድረሰው ፡ ምሥጋና (፬x) ማዳኑን ፡ አስታውቆ ፡ ጽድቁንም ፡ ገለጠ (፪x) ከእኛ ፡ መተላለፍ ፡ ምህረቱ ፡ በለጠ (፪x) በሞገሱ ፡ ጋሻ ፡ እየከለለን (፪x) ከአዳነን ፡ በኋላ ፡ ምህረቱ ፡ ያዘን (፪x) አንድ ፡ ላይ ፡ ተስማሙ ፡ እውነትና ፡ ምህረት (፪x) መግባትም ፡ ተቻለን ፡ እግዚአብሔር ፡ ካለበት (፪x) ጻድቅ ፡ ፈራጅ ፡ ሲሆን ፡ እንከን ፡ የሌለበት (፪x) አልፈረደብኝም ፡ ምህረቱ ፡ አይሎበት (፪x) አዝ እጅግ ፡ የሚምር ፡ የሚራራ አምላክ ፡ ነውና ፡ የእኔ ፡ ጌታ ይድረሰው ፡ ምሥጋና ፡ የእኔ ፡ ጌታ ይድረሰው ፡ ምሥጋና የእኔ ፡ ጌታ ፡ ይድረሰው ፡ ምሥጋና (፬x) ጌታ ፡ እልሃለሁ ፡ አንተን ፡ አመልካለሁ (፪x) አምላክ ፡ እልሃለሁኝ ፡ አንተን ፡ አመልካለሁ (፪x) አንተን ፡ አመልካለሁ ፡ አንተን ፡ አመልካለሁ (፪x) ይገባሃል ፡ የአንደበቴ ፡ ቃል ይገባሃል ፡ የአፌ ፡ ምሥጋና ይገባሃል ፡ ልዘምርልህ ይገባሃል ፡ ላገለግልህ እኔ ፡ አምላክ ፡ እልሃለሁኝ ፡ አንተን ፡ አመልካለሁ (፭x) እስከዛሬ ፡ ተመስገን ፡ ብያለሁ ፡ ተባረክ ፡ ብያለሁ ፡ አሃ ከፍ ፡ በል ፡ ብያለሁ ፡ እስከዛሬ ፡ ተመስገን ፡ ብያለሁ ተባረክ ፡ ብያለሁ ፡ አሃ ፡ ከፍ ፡ በል ፡ ብያለሁ ደግሞ ፡ ዛሬ ፡ ዛሬ ፡ ምን ፡ ልበል ዛሬ ፡ ምን ፡ ልበል ደግሞ ፡ አሁን ፡ አሁን ፡ ምን ፡ ልበል ፡ ጌታ አሁን ፡ ምን ፡ ልበል ደግሞ ፡ ዛሬ ፡ ዛሬ ፡ ምን ፡ ልበል ዛሬ ፡ ምን ፡ ልበል ፡ ዛሬ ፡ ምን ፡ ልበል ይገባሃል ፡ የአንደበቴ ፡ ቃል ይገባሃል ፡ የአፌ ፡ ምሥጋና ይገባሃል ፡ ላገለግልህ ይገባሃል ፡ ልዘምርልህ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ (፬x) ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ (፬x) ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ (፬x)

ቃልኪዳን ጥላሁን · ሁሉም ዘማሪዎች