በታላቅ ግርማ በዙፋኑ ላለው
Betalaq Girma Bezufanu Lalew
ቃልኪዳን ጥላሁን · ጨለማዬን ጌታ እያበራ
ዘማሪ ፡ ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን ርዕስ ፡ በታላቅ ፡ ግርማ ፡ በዙፋኑ ፡ ላለው ጨለማየን ፡ ጌታ ፡ እያበራ በታላቅ ፡ ግርማ ፡ በዙፋኑ ፡ ላለው የምስጋና ፡ ዘውድ ፡ በራሱ ፡ ለጫነው እዘምራለሁ (4x) እኔ ፡ አፌን ፡ አልከፍትም ፡ ለአለም ፡ ክብር እዘምራለሁኝ ፡ ለእግዚአብሔር (2) እቀኝለታለሁ ፡ በአዲስ ፡ አዲስ ፡ ዜማ የምስጋናየ ፡ ድምፅ ፡ በአርያም ፡ ይሰማ (2x) በታላቅ ፡ ግርማ ፡ በዙፋኑ ፡ ላለው የምስጋና ፡ ዘውድ ፡ በራሱ ፡ ለጫነው እዘምራለሁ (4x) በጠዋት ፡ በማታ ፡ በቀን ፡ በሌሊቱ እሰዋለታለሁ ፡ ምስጋናን ፡ በፊቱ (2x) እያደነኩና ፡ እየተደነኩ እግዚአብሔር ፡ አምላኬን ፡ አመልከዋለሁ (2x) በታላቅ ፡ ግርማ ፡ በዙፋኑ ፡ ላለው የምስጋና ፡ ዘውድ ፡ በራሱ ፡ ለጫነው እዘምራለሁ (4x) በታላቅ ፡ ጉባኤ ፡ ሰውም ፡ በበዛበት ለእስራኤል ፡ ቅዱስ ፡ ቅኔን ፡ ልቀኝለት (2x) ከንፈሮቼም ፡ እጅግ ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ አላቸው ዝማሬ ፡ ሲያቀርቡ ፡ ለፈጣሪያቸው (2x) በታላቅ ፡ ግርማ ፡ በዙፋኑ ፡ ላለው የምስጋና ፡ ዘውድ ፡ በራሱ ፡ ለጫነው እዘምራለሁ (4x)

