የሚያረካኝ
Yemiyarekagn
ሀና አላዩ · ንጉሥ ለወደደው · 2016
የሚያረካኝ x 3 እኔን የሚያስደስተኝ ሲከብር ሳየው ኢየሱሴን በህይወቴ ዘመን ጥንት አባቶቼ እንዳስከበሩት ፈቃዱን አርገው እንዳንቀላፉት ፈቃድህ ይሁን በኔም ህይወት ከፍ ብለህ ታይ ጌታ ኢየሱስ የሚያረካኝ x 3 እኔን የሚያስደስተኝ ሲከብር ሳየው ኢየሱሴን በህይወቴ ዘመን ከክፋት ርቆ ክሃጥያት ሸሽቶ በቅድስና ካንተ ጋር ኑሮ በህልውናህ ውስጥ ተጥለቅልቆ መኖር ልዩ ነው ካንተ ጋር አብሮ የሚያረካኝ x 3 እኔን የሚያስደስተኝ ሲከብር ሳየው ኢየሱሴን በህይወቴ ዘመን ፊቴ ያለውን ሩጫ በትግስት ሮጬ የዕምነትን ገድልም ተጋድዬ ያለኝን ሁሉ አፅንቼ ይዤ አክሊል ልቀበል ድልን ነስቼ እርካታዬ ጥማቴ ጉጉቴ ሲከብር ሳየው ነው ኢየሱሴ ልቆ ሲታይ ነው ኢየሱሴ

