Gubae

ረግቻለው

Regechalew

ሀና ፡ ተክሌ · ሀብተ ፡ ሰማይ · 2020

ረግቻለሁ ጌታዬ በፍቅርህ ረግቻለሁ ከእንግዲህ ወደኋላ አልመለስም እኔ በኪዳኑ ደም እኔ ተቀድሻለሁ ለዘላለም ስሙን አወድሳለሁ ረግቻለሁ ጌታዬ በፍቅርህ ረግቻለሁ ከእንግዲህ ወደኋላ አልመለስም እኔ ባዶነቴን አይተህ በምህረትህ ሞላኸኝ ለዘላለም ክብሬ ነህ ኢየሱስ ያዳንከኝ የውስጤን ባዶነት ሰዎች ባያውቁትም አንተ ግን አይተህ አልፈኸኝ አልሄድክም ደግነትህ በዝቶ የራስህ አደረግከኝ ምስጋና ይገባሃል አንተን አወድሳለሁ ረግቻለሁ ጌታዬ በፍቅርህ ረግቻለሁ ከእንግዲህ ወደኋላ አልመለስም እኔ ባዶነቴን አይተህ በምህረትህ ሞላኸኝ ለዘላለም ክብሬ ነህ ኢየሱስ ያዳንከኝ

ሀና ፡ ተክሌ · ሁሉም ዘማሪዎች