Gubae

ቆጠርከኝ

Koterkegn

ሀና ፡ ተክሌ · መሥዋዕት · 2024

በሰው ዘንድ ብረሳ ባይኖረኝ መጠሪያ አንተ ግን ቆጠርከኝ አልከኝ የራስህ እቃ የክብር ስም ሰጠኸኝ በፍቅርህ አቀፍከኝ እግዚአብሔር አምላኬ ልዩ ነህ ያዳንከኝ ቆጠርከኝ ጌታዬ እኔን ቆጠርከኝ በፍቅርህ አቅፈህ የራስህ አደረግከኝ ባዶነቴን አይተህ በምህረትህ ሞላኸኝ ለዘላለም ክብሬ ነህ ኢየሱስ ያዳንከኝ የውስጤን ባዶነት ሰዎች ባያውቁትም አንተ ግን አይተህ አልፈኸኝ አልሄድክም ደግነትህ በዝቶ የራስህ አደረግከኝ ምስጋና ይገባሃል አንተን አወድሳለሁ ቆጠርከኝ ጌታዬ እኔን ቆጠርከኝ በፍቅርህ አቅፈህ የራስህ አደረግከኝ ባዶነቴን አይተህ በምህረትህ ሞላኸኝ ለዘላለም ክብሬ ነህ ኢየሱስ ያዳንከኝ

ሀና ፡ ተክሌ · ሁሉም ዘማሪዎች