Gubae

እየሱስ ፍቅር

Eyesus Fikir

ሀና ፡ ተክሌ · መሥዋዕት · 2024

እየሱስ ፍቅር ነህ ልዩ ነህ ለነፍሴ የውስጤ እረፍት የዘላለም ክብሬ ፍቅርህ ማረከኝ ልቤን ወሰደው ከአንተ በቀር ሌላ መመኪያ የለኝም እየሱስ ፍቅር ነህ እውነተኛ ወዳጄ የውስጤ እረፍት የነፍስ መጠጊያዬ በፍቅርህ አቅፈህ የያዝከኝ አምላኬ ለዘላለም ክብሬ ነህ አንተ ህይወቴ በመስቀል ላይ ውለህ ህይወት የሰጠኸኝ ደምህን አፍስሰህ ከሞት ያዳንከኝ ምን እመልሳለሁ ለዚህ ታላቅ ፍቅርህ ይኸው ምስጋናዬ ይገባሃል ለስምህ እየሱስ ፍቅር ነህ እውነተኛ ወዳጄ የውስጤ እረፍት የነፍስ መጠጊያዬ በፍቅርህ አቅፈህ የያዝከኝ አምላኬ ለዘላለም ክብሬ ነህ አንተ ህይወቴ

ሀና ፡ ተክሌ · ሁሉም ዘማሪዎች