እልፍ እዳ
Elf Eda
ሀና ፡ ተክሌ · መሥዋዕት · 2024
እልፍ እዳ ነበረብኝ ልከፍለው የማልችለው የኃጢአት ዕዳዬን ጌታዬ ነው የከፈለው በመስቀል ላይ ውሎ ነፃ አወጣኝ እኔን ዛሬ በነፃነት ክብሩን እዘምራለሁ እልፍ እዳዬን ከፈለልኝ በእውነት ኢየሱስ አዳነኝ ሰጠኝ ነፃነት ከኃጢአት ባርነት ነፃ ወጥቻለሁ ለዘላለም ለእርሱ እገዛለሁ የማይከፈል ውለታ ነው የዋለልኝ አምላኬ በእርሱ ጽድቅ ተከድኜ ቆሜያለሁ በደስታ የዘላለም ህይወት በእርሱ አግኝቻለሁ ምስጋና ለእርሱ ይሁን ስሙን አከብራለሁ እልፍ እዳዬን ከፈለልኝ በእውነት ኢየሱስ አዳነኝ ሰጠኝ ነፃነት ከኃጢአት ባርነት ነፃ ወጥቻለሁ ለዘላለም ለእርሱ እገዛለሁ

