Gubae

በማለዳ

Bemaleda

ሀና ፡ ተክሌ · መሥዋዕት · 2024

የተገባህ ምስጋና አንተ ነህ የኔ ጌታ የተገባህ ክብር ላንተ ነው የኔ ጌታ በምስጋና ወደፊትህ እቀርባለሁ ላመልክህ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ ይገባሃልና ለስምህ በምስጋና የተፈራህ ገናና አምላክ ነህ ለዑል አምላክ ብንዘምርህ ብንሰግድልህ አይበቃህም አእላፋት ያንተ ፍጥረት ላንተ ክብር ያዜማሉ ቀን ከለሊት ያንተን ስራ በምስጋና ያውጃሉ በማለዳ ምስጋናዬን አበዛለሁ እኔ አበዛለሁ በቀትርም/በሌሊትም ዝማሬዬን አበዛለሁ አበዛለሁ /x፪ ስምህ ሀያል የአማልክቱም አምላክ ገዢ ነህ ታላቅ ጌታ የሆነልህ ሰማይ ምድሩ ምስጋናህ መላዕክቱ ላንተ ሞገስ ላንተ ግርማ ይዘምራሉ ባይገልፅህም በአዲስ ቅኔ ምስጋናህን ያውዳሉ በማለዳ ምስጋናዬን አበዛለሁ እኔ አበዛለሁ በቀትርም/በሌሊትም ዝማሬዬን አበዛለሁ አበዛለሁ /x፪ ለኔ ብዙ ተደርጎልኛል/ሆኖልኛል ኧረ አኔ ብዙ ሆኖልኛል/ተደርጎልኛል ከማመስገን በቀር ምን ይሻለኛል ከማመስገን በቀር ምን ይገልፅልኛል ከማመስገን በቀር ምን ይበጀኛል ከማመስገን በቀር ምን ይገልፅልኛል /x፪ እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን እግዚአብሔርን ያመስግን /x፬

ሀና ፡ ተክሌ · ሁሉም ዘማሪዎች