በጉባኤው መሃል
Begubaiew Mehal
ሀና ፡ ተክሌ · የዘለዓለም ፡ ፈጣሪ · 2013
በጉባኤው መሃል ቆሜ እዘምራለሁ የእግዚአብሔርን ስራ ለሁሉ አወራለሁ ለዘላለም ስሙን አወድሳለሁ ምስጋና ለእርሱ ይሁን ዛሬም ነገም በጉባኤው መሃል ቆሜ እዘምራለሁ የእግዚአብሔርን ስራ ለሁሉ አወራለሁ ባዶነቴን አይተህ በምህረትህ ሞላኸኝ ለዘላለም ክብሬ ነህ ኢየሱስ ያዳንከኝ የውስጤን ባዶነት ሰዎች ባያውቁትም አንተ ግን አይተህ አልፈኸኝ አልሄድክም ደግነትህ በዝቶ የራስህ አደረግከኝ ምስጋና ይገባሃል አንተን አወድሳለሁ በጉባኤው መሃል ቆሜ እዘምራለሁ የእግዚአብሔርን ስራ ለሁሉ አወራለሁ ባዶነቴን አይተህ በምህረትህ ሞላኸኝ ለዘላለም ክብሬ ነህ ኢየሱስ ያዳንከኝ

