አልተረሳሁም
Alteresahum
ሀና ፡ ተክሌ · መሥዋዕት · 2024
ድካሜን አውቀህ አቅም የለሽነቴን ብቻዬን ጥለህ አልሄድክም ጌታዬ በውስጤ ነህና ሰላሜ ህይወቴ ሞገሴ ነህ አንተ አጽናኝ ረዳቴ አልተረሳሁም እኔ አልተረሳሁም የሚተወኝ የለም ደግ ጠባቂ አለኝ በፍቅሩ አቅፎ የያዘኝ አምላኬ ለዘላለም አለ ከእኔ ጋር ወዳጄ ሰዎች ቢተዉኝ ወዳጅ ቢርቀኝ የማይተወኝ ጌታ ኢየሱስ አለኝ የውስጤን አዋቂ ረዳት የዘመኑ የማይለየኝ አባት እውነተኛው አልተረሳሁም እኔ አልተረሳሁም የሚተወኝ የለም ደግ ጠባቂ አለኝ በፍቅሩ አቅፎ የያዘኝ አምላኬ ለዘላለም አለ ከእኔ ጋር ወዳጄ በስምህ ጠርተህ የራስህ አድርገኸኛል ከጠፋሁበት ምድረበዳ ፈልገኸኛል የክብር ልብስ አልብሰህ እምባዬን አብሰሃል ለዘላለም ክብሬ ነህ ኢየሱስ ጋሻዬ አልተረሳሁም እኔ አልተረሳሁም የሚተወኝ የለም ደግ ጠባቂ አለኝ በፍቅሩ አቅፎ የያዘኝ አምላኬ ለዘላለም አለ ከእኔ ጋር ወዳጄ

