Yehie New Egziabhier
ጌታያውቃል እና ብሩክታዊት · ምድር አለፈላት
አዝ፦ ይሄ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ የደረሰው ከጠበኩት ፡ በላይ ፡ ድንቅን ፡ ያደረገው ስለዚህ ፡ በፊቱ ፡ ምሥጋናን ፡ እሰዋለሁ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ እላለሁ (፪x) ምን ፡ እላለሁ ፡ ምሥጋና ፡ ለእርሱ ፡ ሰጣለሁ ምን ፡ እላለሁ ፡ ምሥጋና ፡ አበዛለሁ (፪x) ፀሐይ ፡ ምትወጣ ፡ በስተምስራቅ ፡ በኩል ሲመሽባት ፡ ደግሞ ፡ በስተምዕራብ ፡ ብትሆን ማንም ፡ አይገረምም ፡ በነዚህ ፡ ድርጊቷ ወግና ፡ ስርአቷ ፡ ልክ ፡ ከጥንት ፡ ፍጥረቷ አንድ ፡ ቀን ፡ በደቡብ ፡ ብትወጣ ፡ በድንገት ሲመሽባት ፡ ደግሞ ፡ ሰሜንን ፡ ብትመርጥ ያኔ ፡ እንግዳ ፡ ነገር ፡ ለሁሉም ፡ ይሆናል ለእኔ ፡ ግን ፡ አምላኬ ፡ ከዚህ ፡ በላይ ፡ አድርጓል ጉድ ፡ ተባለ ፡ ሆኖ ፡ ያልተጠበቀ ተሰራልኝ ፡ በዓለም ፡ ያልታወቀ እርሱ ፡ ሚለው ፡ የመዳኔ ፡ ነገር ከሞት ፡ የመትረፌ ፡ አያልቅም ፡ ቢነገር (፬x) አዝ፦ ይሄ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ የደረሰው ከጠበኩት ፡ በላይ ፡ ድንቅን ፡ ያደረገው ስለዚህ ፡ በፊቱ ፡ ምሥጋናን ፡ እሰዋለሁ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ እላለሁ ምን ፡ እላለሁ ፡ ምሥጋና ፡ ለእርሱ ፡ ሰጣለሁ ምን ፡ እላለሁ ፡ ምሥጋና ፡ አበዛለሁ (፪x) እንዲህ ፡ በቀላሉ ፡ እንደዋዛ ፡ ታልፎ ሊተው ፡ አይቻልም ፡ አያስቀምጥ ፡ አርፎ ውስጡ ፡ የተቀመጠው ፡ ምህረቱ ፡ የገባው ይነዘንዘዋል ፡ ቀን ፡ ከሌት ፡ ውለታው ቢያቅተኝ ፡ ቢቸግረኝ ፡ ዝም ፡ ማለት ጉባኤ ፡ መጣሁኝ ፡ ሕዝቡ ፡ ባለበት እኔ ፡ እያስታወስኩኝ ፡ ያረገውን ፡ ስራ አምልኮን ፡ ልሰዋ ፡ ከጉባኤው ፡ ጋራ የገባው ፡ ሰው ፡ የተደረገለት ያላስቻለው ፡ ውለታው ፡ ያለበት ይነሳና ፡ አብሮኝ ፡ ከፍ ፡ ያድርገው ምህረትና ፡ ፍቅር ፡ እሰከ ፡ ዘለዓለም ፡ ነው (፬x) አዝ፦ ይሄ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ የደረሰው ከጠበኩት ፡ በላይ ፡ ድንቅን ፡ ያደረገው ስለዚህ ፡ በፊቱ ፡ ምሥጋናን ፡ እሰዋለሁ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ እላለሁ ምን ፡ እላለሁ ፡ ምሥጋና ፡ ለእርሱ ፡ ሰጣለሁ ምን ፡ እላለሁ ፡ ምሥጋና ፡ አበዛለሁ (፪x) በመስቀል ፡ ላይ ፡ ለእኔ ፡ የሰራውን ፡ ስራ ቀንም ፡ ሆነ ፡ ሌሊት ፡ ሁልጊዜ ፡ ባወራ ቃላት ፡ አይበቃኝም ፡ ዓረፍተ ፡ ነገሮች እንጂ ፡ የእርሱ ፡ ስራ ፡ አያልቅም ፡ እንደ ፡ ሌሎች ዕልልታና ፡ አምልኮ ፡ ላምላኬ ፡ ሳላስቀር በምሥጋና ፡ ፊቱ ፡ ከመቅረብ ፡ በስተቀር ሌላ ፡ ምን ፡ ምርጫ ፡ አለኝ ፡ ለእርሱ ፡ የምሰጠው ገና ፡ ጨማምሬ ፡ ምሥጋና ፡ እሰዋለሁ መቼ ፡ ያልቃል ፡ ቢወራ ፡ ቢወራ ተናግሬ ፡ መቼም ፡ አያበቃ እርሱም ፡ ቢሆን ፡ የመዳኔ ፡ ነገር የመስቀሉ ፡ ስራ ፡ አያልቅም ፡ ቢነገር (፬x) የኢየሱስ ፡ ስራ ፡ አያልቅም ፡ ቢነገር (፪x) አዝ፦ ይሄ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ የደረሰው ከጠበኩት ፡ በላይ ፡ ድንቅን ፡ ያደረገው ስለዚህ ፡ በፊቱ ፡ ምሥጋናን ፡ እሰዋለሁ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ እላለሁ ምን ፡ እላለሁ ፡ ምሥጋና ፡ ለእርሱ ፡ ሰጣለሁ ምን ፡ እላለሁ ፡ ምሥጋና ፡ አበዛለሁ (፪x) "ጸሎት ፡ ሰዓት" አዝ፦ አተገመትም ፡ በሊቃናት ፡ ብዛት አትወሰንም ፡ በአእምሮ ፡ ስፋት አትገመትም ፡ በሺ ፡ ቃላት ፡ ብዛት አትወሰንም ፡ በጠቢባን ፡ ጥበብ አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ ፤ በላይ ፡ ነህ (፪x) የችግር ፡ ቋጠሮ ፡ ውስብስብ ፡ ሲልብህ መግቢያ ፡ መውጫ ፡ ጠፍቶህ ፡ ግራ ፡ ሲያጋባህ አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ ደግሞ ፡ ሲፈታታ ፡ ችግር ፡ ሁሉ ፡ ሲተን የትላንት ፡ ጨለማ ፡ እንደጉም ፡ ሲበተን አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ አዝ፦ አተገመትም ፡ በሊቃናት ፡ ብዛት አትወሰንም ፡ በአእምሮ ፡ ስፋት አትገመትም ፡ በሺ ፡ ቃላት ፡ ብዛት አትወሰንም ፡ በጠቢባን ፡ ጥበብ አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ ፤ በላይ ፡ ነህ (፪x) አንተን ፡ እንዳላመልክ ፡ ከፍታው ፡ ዝቅታ ከቶ ፡ አያግደኝም ፡ አይጠፋኝ ፡ ዕልልታ አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ ውስጤ ፡ ቅኔ ፡ ሞልቷል ፡ ከገጠመኝ ፡ በላይ አምላኬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህና ፡ ኤልሻዳይ አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ አዝ፦ አተገመትም ፡ በሊቃናት ፡ ብዛት አትወሰንም ፡ በአእምሮ ፡ ስፋት አትገመትም ፡ በሺ ፡ ቃላት ፡ ብዛት አትወሰንም ፡ በጠቢባን ፡ ጥበብ አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ ፤ በላይ ፡ ነህ (፪x) ሁሉም ፡ ነገር ፡ ጠፍቶ ፡ በቤቴ ፡ የሚበላ ያልጠበኩት ፡ ነገር ፡ ሲሆንብኝ ፡ ሌላ አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ ደግሞ ፡ በጐጆዬ ፡ በረከት ፡ ሲሞላ ሁሉም ፡ ነገር ፡ ሞልቶ ፡ ሲተርፈኝ ፡ ለሌላ አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ አዝ፦ አተገመትም ፡ በሊቃናት ፡ ብዛት አትወሰንም ፡ በአእምሮ ፡ ስፋት አትገመትም ፡ በሺ ፡ ቃላት ፡ ብዛት አትወሰንም ፡ በጠቢባን ፡ ጥበብ አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ ፤ በላይ ፡ ነህ (፪x) ሲሞላ ፡ ዘምሬ ፡ ሲጐድል ፡ ላላለቅስ በምንም ፡ ሁኔታ ፡ አምልኮ ፡ አልቀንስም አንተ ፡ ከሁሉም ፡ በላይ ፡ ነህ እታመንሃለሁ ፡ በምሥጋና ፡ ሆኜ ድል ፡ እንደምትሰጠኝ ፡ በስምህ ፡ አምኜ አንተ ፡ ከሁሉም ፡ በላይ ፡ ነህ አዝ፦ አተገመትም ፡ በሊቃናት ፡ ብዛት አትወሰንም ፡ በአእምሮ ፡ ስፋት አትገመትም ፡ በሺ ፡ ቃላት ፡ ብዛት አትወሰንም ፡ በጠቢባን ፡ ጥበብ አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ ፤ በላይ ፡ ነህ (፪x)

