Mesqeleh Ser
ጌታያውቃል እና ብሩክታዊት · Ye11gnaw Seat Yetselot Teri
ተስፋ ፡ ቆርጬ ፡ ወደኋላዬ ፡ አልልም በጥቂቱ ፡ ዝዬ ፡ አልመለስም ብትገድለኝም ፡ ብታድነኝም ብትሰጠኝም ፡ ብትነሳኝም እጅህን ፡ እጠብቃለሁ ፡ ከፊትህ ፡ አልሄድም አንተን ፡ የለመነህ ፡ በፊትህ ፡ ጠብቆ ሁሉን ፡ እንደምትችል ፡ እንደምትሰጥ ፡ አውቆ ጊዜውን ፡ ብታረዝምም ፡ እምነቱን ፡ ልትፈትን እርሱን ፡ የጠበቀው ፡ መች ፡ አጣው ፡ ባርኮቱን አግኝቷል ፡ ከጌታ ፡ አጽንቶ ፡ እምነቱን እኔም ፡ መስቀልህ ፡ ስር ፡ ሆኜ ፡ እጠብቃለሁ ምን ፡ እንደምትሰራ ፡ እጅህን ፡ አያለሁ ጉልበቴን ፡ በፊትህ ፡ አምበረክካለሁ ቃሌንም ፡ በቤትህ ፡ ዝም ፡ አሰኘዋለሁ አንተ ፡ ምትሰራውን ፡ በሙሉ ፡ አያለሁ አንዲት ፡ ከነአናዊት ፡ ሴት ፡ ወደ ፡ ኢየሱስ ፡ መጥታ 'የዳዊት ፡ ልጅ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ልጄ ፡ በእርኩስ ፡ መንፈስ ተይዛ ፡ ትስቃያለችና ፡ እባክህ ፡ እራራልኝ' ፡ እያለች ፡ ጮኸች እርሱ ፡ ግን ፡ አንድም ፡ ቃል ፡ ሳይመልስላት ፡ ዝም ፡ አለ በዚያን ፡ ጊዜ ፡ ደቀ ፡ መዛሙርቱ ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ ቀረብ ፡ ብለው 'ይሂች ፡ ሴት ፡ እየተከተለችን ፡ ስለምትጮህ ፡ እባክህ ፡ አሰናብታት' ፡ ሲሉ ፡ ለመኑት እርሱም ፡ 'እኔ ፡ የተላኩት ፡ ከእስራኤል ፡ ቤት ፡ እንደበጐች ፡ ለጠፉት ፡ ብቻ ፡ ነው' ሲል ፡ መለሰ። ሴትዬዋ ፡ ግን ፡ ቀርባ ፡ በእግሩ ፡ ስር ፡ ተንበረከከችና 'ጌታ ፡ ሆይ ፡ እባክህ ፡ እርዳኝ ፡ አለችው'። ኢየሱስም ፡ 'የልጆችን ፡ እንጀራ ፡ ወስዶ ፡ ለውሾች ፡ መጣል ፡ የተገባ ፡ አይደለም' ፡ አለ። እርሷም ፡ 'ጌታ ፡ ሆይ ፡ እርግጥ ፡ ነው። ነገር ፡ ግን ፡ ውሾችም ፡ እኮ ከጌቶቻቸው ፡ ማዐድ ፡ የወደቀውን ፡ ፍርፋሪ ፡ ይበላሉ' ፡ አለችው። በዚያን ፡ ጊዜ ፡ ኢየሱስ ፡ 'አንቺ ፡ ሴት ፡ እምነትች ፡ ትልቅ ፡ ነው። ስለዚህ ፡ እንደፍላጐትሽ ፡ ይሁንልሽ ፡ አላት'። የሴትየዋም ፡ ልጅ ፡ በዚያን ፡ ሰዓት ፡ ዳነች። በለእርሱን ፡ የጠበቀ ፡ ፍሬዋን ፡ ይበላል ከጌታው ፡ ሚጠብቅ ፡ እርሱ ፡ ደግሞ ፡ ይከብራል እኔም ፡ ከአንተ ፡ ብቻ ፡ እጠብቃለሁኝ የአማረውን ፡ ፍሬ ፡ ለመብላት ፡ ጓጓሁኝ አይቀርም ፡ አንድ ፡ ቀን ፡ ደግሞ ፡ እከብራለሁኝ ብትሰጠኝም ፡ ብትነሳኝም እጅህን ፡ እጠብቃለሁ ፡ ከፊትህ ፡ አልሄድም ቃሌንም ፡ በቤትህ ፡ ዝም ፡ አሰኘዋለሁ አንተ ፡ ምትሰራውን ፡ በሙሉ ፡ አያለሁ ተስፋ ፡ ቆርጬ ፡ ወደኋላዬ ፡ አልልም በጥቂቱ ፡ ዝዬ ፡ አልመለስም ብትገድለኝም ፡ ብታድነኝም ብትሰጠኝም ፡ ብትነሳኝም እጅህን ፡ እጠብቃለሁ ፡ ከፊትህ ፡ አልሄድም አንተን ፡ የለመነህ ፡ በፊትህ ፡ ጠብቆ ሁሉን ፡ እንደምትችል ፡ እንደምትሰጥ ፡ አውቆ ጊዜውን ፡ ብታረዝምም ፡ እምነቱን ፡ ልትፈትን እርሱን ፡ የጠበቀው ፡ መች ፡ አጣው ፡ ባርኮቱን አግኝቷል ፡ ከጌታ ፡ አጽንቶ ፡ እምነቱን እኔም ፡ መስቀልህ ፡ ስር ፡ ሆኜ ፡ እጠብቃለሁ ምን ፡ እንደምትሰራ ፡ እጅህን ፡ አያለሁ ጉልበቴን ፡ በፊትህ ፡ አምበረክካለሁ ቃሌንም ፡ በቤትህ ፡ ዝም ፡ አሰኘዋለሁ አንተ ፡ ምትሰራውን ፡ በሙሉ ፡ አያለሁ አንዲት ፡ ከነአናዊት ፡ ሴት ፡ ወደ ፡ ኢየሱስ ፡ መጥታ 'የዳዊት ፡ ልጅ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ልጄ ፡ በእርኩስ ፡ መንፈስ ተይዛ ፡ ትስቃያለችና ፡ እባክህ ፡ እራራልኝ' ፡ እያለች ፡ ጮኸች እርሱ ፡ ግን ፡ አንድም ፡ ቃል ፡ ሳይመልስላት ፡ ዝም ፡ አለ በዚያን ፡ ጊዜ ፡ ደቀ ፡ መዛሙርቱ ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ ቀረብ ፡ ብለው 'ይሂች ፡ ሴት ፡ እየተከተለችን ፡ ስለምትጮህ ፡ እባክህ ፡ አሰናብታት' ፡ ሲሉ ፡ ለመኑት እርሱም ፡ 'እኔ ፡ የተላኩት ፡ ከእስራኤል ፡ ቤት ፡ እንደበጐች ፡ ለጠፉት ፡ ብቻ ፡ ነው' ሲል ፡ መለሰ። ሴትዬዋ ፡ ግን ፡ ቀርባ ፡ በእግሩ ፡ ስር ፡ ተንበረከከችና 'ጌታ ፡ ሆይ ፡ እባክህ ፡ እርዳኝ ፡ አለችው'። ኢየሱስም ፡ 'የልጆችን ፡ እንጀራ ፡ ወስዶ ፡ ለውሾች ፡ መጣል ፡ የተገባ ፡ አይደለም' ፡ አለ። እርሷም ፡ 'ጌታ ፡ ሆይ ፡ እርግጥ ፡ ነው። ነገር ፡ ግን ፡ ውሾችም ፡ እኮ ከጌቶቻቸው ፡ ማዐድ ፡ የወደቀውን ፡ ፍርፋሪ ፡ ይበላሉ' ፡ አለችው። በዚያን ፡ ጊዜ ፡ ኢየሱስ ፡ 'አንቺ ፡ ሴት ፡ እምነትች ፡ ትልቅ ፡ ነው። ስለዚህ ፡ እንደፍላጐትሽ ፡ ይሁንልሽ ፡ አላት'። የሴትየዋም ፡ ልጅ ፡ በዚያን ፡ ሰዓት ፡ ዳነች። በለእርሱን ፡ የጠበቀ ፡ ፍሬዋን ፡ ይበላል ከጌታው ፡ ሚጠብቅ ፡ እርሱ ፡ ደግሞ ፡ ይከብራል እኔም ፡ ከአንተ ፡ ብቻ ፡ እጠብቃለሁኝ የአማረውን ፡ ፍሬ ፡ ለመብላት ፡ ጓጓሁኝ አይቀርም ፡ አንድ ፡ ቀን ፡ ደግሞ ፡ እከብራለሁኝ ብትሰጠኝም ፡ ብትነሳኝም እጅህን ፡ እጠብቃለሁ ፡ ከፊትህ ፡ አልሄድም ቃሌንም ፡ በቤትህ ፡ ዝም ፡ አሰኘዋለሁ አንተ ፡ ምትሰራውን ፡ በሙሉ ፡ አያለሁ

