Gubae

Mesgana

ጌታያውቃል እና ብሩክታዊት · ምድር አለፈላት

አዝ፦ በማለዳ ፡ ምሥጋናዬን ፡ አበዛለሁ በቀትርም ሌላ ፡ ክብር ፡ እጨምራለሁ ጊዜው ፡ መምሸቱ ፡ ውድቅት ፡ ሌሊቱ አያግደኝም ፡ ከመቅረብ ፡ ፊቱ ሥሙን ፡ ልባርከው ፡ ሁሌ ፡ ጠራዋለሁ ክብር ፡ እያበዛሁ ፡ አስደስተዋለሁ ሥሙን ፡ ልባርከው ፡ ሁሌ ፡ ጠራዋለሁ ድምጼን ፡ እያሰማሁ ፡ አስደስተዋለሁ አፌን ፡ በምሥጋና ፡ ሞልተኸዋልና እግዚአብሔር ፡ እኔ ፡ ልባርክህ (፪x) እናገር ፡ የምችለውን ፡ ይህን ፡ ነውና እግዚአብሔር ፡ እኔ ፡ ልባርክህ (፪x) ያዘነ ፡ በፊትህ ፡ አይገኝምና እግዚአብሔር ፡ እኔ ፡ ልባርክህ (፪x) በፊትህ ፡ ቃል ፡ ደስታ ፡ ይጠግባልና እግዚአብሔር ፡ እኔ ፡ ልባርክህ (፪x) አዝ፦ በማለዳ ፡ ምሥጋናዬን ፡ አበዛለሁ በቀትርም ፡ ሌላ ፡ ክብር ፡ እጨምራለሁ ጊዜው ፡ መምሸቱ ፡ ውድቅት ፡ ሌሊቱ አያግደኝም ፡ ከመቅረብ ፡ ፊቱ ሥሙን ፡ ልባርከው ፡ ሁሌ ፡ ጠራዋለሁ ክብር ፡ እያበዛሁ ፡ አስደስተዋለሁ ሥሙን ፡ ልባርከው ፡ ሁሌ ፡ ጠራዋለሁ ድምጼን ፡ እያሰማሁ ፡ አስደስተዋለሁ የጐበጠው ፡ ሁሉ ፡ ቀና ፡ ይላልና እግዚአብሔር ፡ እኔ ፡ ልባርክህ (፪x) ለሰው ፡ የማይቻል ፡ ይቻልሃልና እግዚአብሔር ፡ እኔ ፡ ልባርክህ (፪x) ለቃልህ ፡ የማይታዘዝ ፡ አንድም ፡ የለምና እግዚአብሔር ፡ እኔ ፡ ልባርክህ (፪x) ብቻህን ፡ ተዓምራት ፡ ታደርጋለህና እግዚአብሔር ፡ እኔ ፡ ልባርክህ (፪x) አዝ፦ በማለዳ ፡ ምሥጋናዬን ፡ አበዛለሁ በቀትርም ፡ ሌላ ፡ ክብር ፡ እጨምራለሁ ጊዜው ፡ መምሸቱ ፡ ውድቅት ፡ ሌሊቱ አያግደኝም ፡ ከመቅረብ ፡ ፊቱ ሥሙን ፡ ልባርከው ፡ ሁሌ ፡ ጠራዋለሁ ክብር ፡ እያበዛሁ ፡ አስደስተዋለሁ ሥሙን ፡ ልባርከው ፡ ሁሌ ፡ ጠራዋለሁ ድምጼን ፡ እያሰማሁ ፡ አስደስተዋለሁ ሕዝብህ ፡ ወደ ፡ እረፍት ፡ ይገባልና እግዚአብሔር ፡ እኔ ፡ ልባርክህ (፪x) እርዳታህም ፡ ከላይ ፡ ይመጣልና እግዚአብሔር ፡ እኔ ፡ ልባርክህ (፪x) በሰንበትም ፡ ችግር ፡ አይገኝምና እግዚአብሔር ፡ እኔ ፡ ልባርክህ (፪x) ሁሉ ፡ በሚያርፍበት ፡ ትሰራለህና እግዚአብሔር ፡ እኔ ፡ ልባርክህ (፪x) አዝ፦ በማለዳ ፡ ምሥጋናዬን ፡ አበዛለሁ በቀጥትርም ፡ ሌላ ፡ ክብር ፡ እጨምራለሁ ጊዜው ፡ መምሸቱ ፡ ውድቅት ፡ ሌሊቱ አያግደኝም ፡ ከመቅረብ ፡ ፊቱ ሥሙን ፡ ልባርከው ፡ ሁሌ ፡ ጠራዋለሁ ክብር ፡ እያበዛሁ ፡ አስደስተዋለሁ ሥሙን ፡ ልባርከው ፡ ሁሌ ፡ ጠራዋለሁ ድምጼን ፡ እያሰማሁ ፡ አስደስተዋለሁ

ጌታያውቃል እና ብሩክታዊት · ሁሉም ዘማሪዎች