Ategemetem
ጌታያውቃል እና ብሩክታዊት · ምድር አለፈላት
አዝ፦ አተገመትም ፡ በእኔ ፡ ቃላት ፡ ብዛት አትወሰንም ፡ በአእምሮ ፡ ስፋት አትገመትም ፡ በሺህ ፡ ቃላት ፡ ብዛት አትወሰንም ፡ በጠቢባን ፡ ጥበብ አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ ፤ በላይ ፡ ነህ (፪x) የችግር ፡ ቋጠሮ ፡ ውስብስብ ፡ ሲልብኝ መግቢያ ፡ መውጫ ፡ ጠፍቶህ ፡ ግራ ፡ ሲያጋባኝ አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ ደግሞ ፡ ሲፈታታ ፡ ችግር ፡ ሁሉ ፡ ሲተን የትላንት ፡ ጨለማ ፡ እንደጉም ፡ ሲበተን አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ አዝ፦ አተገመትም ፡ በእኔ ፡ ቃላት ፡ ብዛት አትወሰንም ፡ በአእምሮ ፡ ስፋት አትገመትም ፡ በሺህ ፡ ቃላት ፡ ብዛት አትወሰንም ፡ በጠቢባን ፡ ጥበብ አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ ፤ በላይ ፡ ነህ (፪x) አንተን ፡ እንዳላመልክ ፡ ከፍታው ፡ ዝቅታ ከቶ ፡ አያግደኝም ፡ አይጠፋኝ ፡ ዕልልታ አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ ውስጤ ፡ ቅኔ ፡ ሞልቷል ፡ ከገጠመኝ ፡ በላይ አምላኬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህና ፡ ኤልሻዳይ አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ አዝ፦ አተገመትም ፡ በእኔ ፡ ቃላት ፡ ብዛት አትወሰንም ፡ በአእምሮ ፡ ስፋት አትገመትም ፡ በሺህ ፡ ቃላት ፡ ብዛት አትወሰንም ፡ በጠቢባን ፡ ጥበብ አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ ፤ በላይ ፡ ነህ (፪x) ሁሉም ፡ ነገር ፡ ጠፍቶ ፡ በቤቴ ፡ የሚበላ ያልጠበኩት ፡ ነገር ፡ ሲሆንብኝ ፡ ሌላ አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ ደግሞ ፡ በጐጆዬ ፡ በረከት ፡ ሲሞላ ሁሉም ፡ ነገር ፡ ሞልቶ ፡ ሲተርፈኝ ፡ ለሌላ አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ አዝ፦ አተገመትም ፡ በእኔ ፡ ቃላት ፡ ብዛት አትወሰንም ፡ በአእምሮ ፡ ስፋት አትገመትም ፡ በሺህ ፡ ቃላት ፡ ብዛት አትወሰንም ፡ በጠቢባን ፡ ጥበብ አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ ፤ በላይ ፡ ነህ (፪x) ሲሞላ ፡ ዘምሬ ፡ ሲጐድል ፡ ላላለቅስ በምንም ፡ ሁኔታ ፡ አምልኮ ፡ አልቀንስም አንተ ፡ ከሁሉም ፡ በላይ ፡ ነህ እታመንሃለሁ ፡ በምሥጋና ፡ ሆኜ ድል ፡ እንደምትሰጠኝ ፡ በስምህ ፡ አምኜ አንተ ፡ ከሁሉም ፡ በላይ ፡ ነህ አዝ፦ አተገመትም ፡ በእኔ ፡ ቃላት ፡ ብዛት አትወሰንም ፡ በአእምሮ ፡ ስፋት አትገመትም ፡ በሺህ ፡ ቃላት ፡ ብዛት አትወሰንም ፡ በጠቢባን ፡ ጥበብ አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ ፤ በላይ ፡ ነህ (፪x)

