ዘምር አለኝ
Zemer Alegn
ኤፍሬም አለሙ · አቻ የሌለው · 2010
የሲኦል ፡ በር ፡ ሲዘጋ ፡ ለእኔ ፡ ሌቱ ፡ ሲነጋ (ሲነጋ) ፡ ሲነጋ (ሲነጋ) ጠላቴ ፡ ሲመሽበት ፡ ለማጁ ፡ ሰው ፡ በራለት ፡ ነጋለት (ነጋለት) ፡ በራለት (በራለት) ደሙ ፡ ነው ፡ ምልክቴ ፡ አይገባም ፡ ሞት ፡ እቤቴ ፤ ከቤቴ (ከቤቴ) ፡ እቤቴ (ከቤቴ) ያሳረገኝ ፡ ደሙ ፡ ነው ፡ ስለዚህ ፡ እዘምራለሁኝ ፡ ለጌታ (ለጌታ) ፡ በደስታ (በደስታ) ምልክት ፡ አለብኝ ፡ የኢየሱስ ፡ ደም ፡ በግምባሬ ይፈራኛል ፡ ጠላት ፡ ከቶ ፡ አይቀርብም ፡ በሰፈሬ በአጠገቤ ፡ ሺ ፡ በቀኝ ፡ አስር ፡ ሺ ፡ እየጣለልኝ ፡ ሆንኩኝ ፡ ድል ፡ ነሺ ዙሪያዬ ፡ ስሜ ፡ በደሙ ፡ ታጥሯል ፡ ቅዱስ ፡ መንፈሱ ፡ ይጠብቀኛል በድል ፡ ወጥቼ ፡ በድል ፡ እገባለሁ ፡ የእኔ ፡ ከለላ ፡ የእሳት ፡ ቅጥር ፡ ነው ጠላት ፡ የጻፈው ፡ የሞት ፡ ደብዳቤ ተቀዶ ፡ ሳየው ፡ ደስ ፡ አለው ፡ ልቤ (ደስ ፡ አለው ፡ ልቤ) ጠላቴን ፡ ጥሎ ፡ ስላሳየኝ ልቤም ፡ በደስታ ፡ ዘምር ፡ አለኝ (ዘምር ፡ አለኝ)

