መለሰኝ
Melesegn
ኤፍሬም አለሙ · አቻ የሌለው · 2010
እረጅሙን ፡ ጐዳና ፡ በጽድቅ ፡ እንዳልሄድኩኝ አንተን ፡ እንዳላሳዝን ፡ ፊትህ ፡ እንደማልኩኝ ዛሬ ፡ ምነው ፡ ጠፋኝ ፡ አቅም ፡ አጠረኝኝ እኔ ፡ ነኝ ፡ ጥፋተኛ ፡ እኔን ፡ እኔን ፡ ማረኝ ዕንቁዬን ፡ ሜዳ ፡ ጥዬው ፡ ብቻዬን ፡ ቀረሁኝ ጌታ ፡ ሆይ ፡ መልሰኝ ፡ ምህረት ፡ አድርግልኝ አዝ፦ መልሰኝ ፡ ወደድሮዬ ፣ መልሰኝ ፡ ወዳስተማርከኝ መልሰኝ ፡ ወደጓዳዬ ፣ መልሰኝ ፡ ወደነገርከኝ አንተን ፡ ተጣልቼ ፡ እንዴት ፡ እሆናለሁ ከአንተ ፡ ተስማምቼ ፡ እኔስ ፡ እኖራለሁ ስታበይ ፡ ገሥጸኝ ፡፡ ሳጠፋ ፡ ቅጣኝ መንፈስህን ፡ ከእኔ ፡ አትውሰድብኝ አንተ ፡ ዝም ፡ ካልከኝ ፡ ምንስ ፡ ይውጠኛል የአንተ ፡ ዝምታ ፡ እኮ ፡ አፍ ፡ አለው ፡ ያወራል ብቻ ፡ ይሁን ፡ እንጂ ፡ የነገርከኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ያልከኝ እኔስ ፡ ከሃሳብህ ፡ ጋር ፡ እስማማለሁ ፡ ይሁን ፡ እንዳልከኝ (፪x) ብዙ ፡ የለፋሁበት ፡ ያከማቸሁት ፡ ሃብቴ ከእጄ ፡ ላይ ፡ ተበተነ ፡ ሳላውቀው ፡ ከጥማቴ የተቀደስኩለት ፡ ከዳኝ ፡ ማንነቴ አወይ ፡ አለመታዘዝ ፡ አሻፈረኝ ፡ ማለቴ አይረባህም ፡ ስትለኝ ፡ አንተን ፡ አለመስማቴ ዛሬ ፡ ግን ፡ ገብቶኛል ፡ አድሰኝ፡ አባቴ አዝ፦ መልሰኝ ፡ ወደድሮዬ ፣ መልሰኝ ፡ ወዳስተማርከኝ መልሰኝ ፡ ወደጓዳዬ ፣ መልሰኝ ፡ ወደነገርከኝ አንተን ፡ ተጣልቼ ፡ እንዴት ፡ እሆናለሁ ከአንተ ፡ ተስማምቼ ፡ እኔስ ፡ እኖራለሁ ጴጥሮስ፡ ሓዋርያው ፡ አልክድህም ፡ ያለው ዶሮ ፡ ሳይጮህ ፡ በፊት ፡ ሶስት ፡ ጊዜ ፡ ነው ፡ የካደው ነገር ፡ ግን ፡ ምህረትህ ፡ እጅግ ፡ ስለበዛ አስበህ ፡ ለወጥከው ፡ ሰው ፡ አደረከው ፡ ጌታ ብቻ ፡ ይሁን ፡ እንጂ ፡ የነገርከኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ያልከኝ እኔስ ፡ ከሃሳብህ ፡ ጋር ፡ እስማማለሁ ፡ ይሁን ፡ እንዳልከኝ (፪x)

