ልዘምርለት
Lezemerelet
ኤፍሬም አለሙ · ለማን አዳልቶ
ጠብቆኝ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ዛሬ ፡ ያለሁት ፡ ከጠላቴ ፡ ዛቻ መቼ ፡ እወጣው ፡ ነበር ፡ ለብቻዬ ፡ ያንን ፡ ሁሉ ፡ ጣጣ በጐኔ ፡ ሳይርቀኝ ፡ ሳይለየኝ ፡ ከክፉ ፡ ጠብቆ መንገዴን ፡ አንቅቶ ፡ ጀምሬያለሁ ፡ የሰላምን ፡ ጉዞ በክፉ ፡ ቀን ፡ ያልተለየኝ በሃዘኔ ፡ ከቶ ፡ ያልሸሸኝ እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ አለኝ እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ አለኝ በክፉ ፡ ቀን ፡ ያልተለየኝ (፪x) ብዘምርለት ፡ መች ፡ ይበቃዋል ፡ ብዘምርለት (፬x) ካረገው ፡ ጋራ ፡ መች ፡ ሊወዳደር ፡ የእኔ ፡ መዘመር በእስራኤል/በኤፍሬም ፡ ላይ ፡ ሟርትም ፡ አይሰራ ድንጋጤም ፡ ቤቱ ፡ አይገባ እግዚአብሔር ፡ ቅጥር ፡ ሆኖታል በከፍታ ፡ ያዘምረዋል (፬x) እንደ ፡ ትላንትናው ፡ መስሎ ፡ ጠላት ፡ ሊያጠፋኝ ፡ ሲመጣ ዛሬ ፡ ግን ፡ ቤቴ ፡ አለ ፡ ኢየሱሴ ፡ የሰላም ፡ አለቃ ደሙ ፡ በመቃኔ ፡ በጉበእኔ ፡ ላይ ፡ ስለተቀባ አልቻለም ፡ ጠላቴ ፡ እንደድሮ ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ሊጠጋ በክፉ ፡ ቀን ፡ ያልተለየኝ በሃዘኔ ፡ ከቶ ፡ ያልሸሸኝ እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ አለኝ እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ አለኝ በክፉ ፡ ቀን ፡ ያልተለየኝ (፪x) በእስራኤል/በኤፍሬም ፡ ላይ ፡ ሟርትም ፡ አይሰራ ድንጋጤም ፡ ቤቱ ፡ አይገባ እግዚአብሔር ፡ ቅጥር ፡ ሆኖታል በከፍታ ፡ ያዘምረዋል (፬x) ትጠፋለህ ፡ ብሎ ፡ የደገመው ፡ ጠላቴ ፡ የታለ ኧረ ፡ እኔስ ፡ አለሁኝ ፡ በሕይወቴ ፡ ኢየሱስ ፡ ስለለ በአንዳች ፡ አልጨነቅ ፡ አልሸበር ፡ ለነገም ፡ አልፈራ በአንድ ፡ የመጣው ፡ ጠላት ፡ ይበተናል ፡ በሰባት ፡ ጐዳና በክፉ ፡ ቀን ፡ ያልተለየኝ በሃዘኔ ፡ ከቶ ፡ ያልሸሸኝ እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ አለኝ እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ አለኝ በክፉ ፡ ቀን ፡ ያልተለየኝ (፪x) ብዘምርለት ፡ መች ፡ ይበቃዋል ፡ ብዘምርለት (፫x) ካረገው ፡ ጋራ ፡ መች ፡ ሊወዳደር ፡ የእኔ ፡ መዘመር

