ወደ መቅደሱ ስገባ
Wede Mekdesu Segeba
እንድርያስ ሐዋዝ · ወደ መቅደሱ ስገባ · 2010
ወደ መቅደሱ ስገባ ድምጼን ላሰማ በምስጋና በፍቅሩ ስቦ የመከረኝን ባማረ ስፍራ ያስቀመጠኝን ከፍ ላድርገዉ እግዚአብሄርን አንድ ጊዜ አይደለም ሁለት ጊዜ ጌታ የመከረኝ በግሳጼ እንደ እኔማ ቢሆን እንደ ሀጢያቴ የቁጣ ልጅ ነበርኩ ከፍጥረቴ ዛሬ ግን መክሮኝ ሰዉ ሆኛለሁ በመቅደሱ ዉስጥ አዜማለሁ አሁን ዞር ብዬ ከኅላ ሳየዉ መራራዉ ህይወቴ ዛሬ የጣፈጠዉ እንዴት ያለዉን ሰዉን ለወጥከዉ አምላኬ እግዚአብሄር ስራህ ድንቅ ነዉ ገመድ ባማረ ስፍራ ወድቃልኝ ባምላኬ ርስቴ ተዋበችልኝ አንካሳ ነበረኩ መሄድ የማልችል እውርም ነበርኩ ማየት የማልችል የሱስ የሚባል አንድ ወዳጅ አይቶኝ በእጆቹ ዳሶኝ በድንቅ ፈወሰኝ እንደርሱ ያለ የለኝምና ዛሬም ቆሜያለሁ በምስጋና ጌታ እግዚአብሔር እረ እኔ ማን ነኝ ለዚህ የክብር ህይወት ያጨኸኝ አይገባኝም ይህ ለኔ አይደለም ከሰው ሁሉ የማንስ ሃጢያተኛ ነኝ አንተ ካረግከው ምን እላለሁ ይኸው ለክብርህ አዜማለሁ

