ክብር ይሁን
Keber Yihun
እንድርያስ ሐዋዝ · ወደ መቅደሱ ስገባ · 2010
ክብር ይሁን ክብር x8 በላይ በሰማይ ዙፋኑ ላይ በታች በምድር ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን ክብር x4 ሀጢያተኛውን አስበኸዋል በደምህ አጥበህ አንፅተኸዋል ከፃድቃን ማህበር ቀላቅለኸዋል ከሳሹ ጠላት ዲያብሎስ አፍሮአል ለዚህ ለስራህ ምን ይከፈላል ክብር ይሁን ክብር x2 በላይ በሰማይ ዙፋኑ ላይ በታች በምድር ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን ክብር x4 ደረቁን ምድር አረስርሰሀል የተራቆተውን አንተ አልብሰሀል በታሪክ ማህደር ያልታወቀውን አንተ አስጠግትህ አገነንክ ስሙን ጌታዬ ክብሩ ለአንተ ይሁን ዙፋኑ ከጥንት ከዘላለም ብርቱ ተዋጊ እንዳንተ የለም የጠላት ምክሩን አፍርሰኸዋል ባንድላይ መጥተው ተበትነዋል ጌታ ሆይ ላንተ ክብር ይገባሀል ክብር ይሁን ክብር x2 በላይ በሰማይ ዙፋኑ ላይ በታች በምድር ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን ክብር x4 አዝ፦ በኃይል ፡ ቢሆን ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ ኃይል በክብር ፡ ቢሆን ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ ክቡር በስልጣን ፡ ቢሆን ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ ባለስልጣን እግዚአብሔር ፡ እግዚአብሔር ፡ ኃያል (፪x) ክብር ፡ ይሻራል ፡ ውበት ፡ ይጠፋል ሃብትም ፡ ይበናል አበባው ፡ ረግፎ ፡ ሲጠወላልግ ትላንት ፡ ያየነው ፡ ለዛሬ ፡ ሲደርቅ አንተ ፡ ብቻ ፡ አትለዋወጥ እጅግ ፡ ዕጹብ ፡ ድንቅ አዝ፦ በኃይል ፡ ቢሆን ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ ኃይል በክብር ፡ ቢሆን ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ ክቡር በስልጣን ፡ ቢሆን ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ ባለስልጣን እግዚአብሔር ፡ እግዚአብሔር ፡ ኃያል (፪x) በምድር ፡ ክበቦች ፡ ላይ ፡ የሚራመድ ሰማይ ፡ ተቀምጦ ፡ ምድር ፡ የሚረግጥ ከፍ ፡ ካለው ፡ በላይ ፡ ከፍ ፡ ያለ ፡ ጌታ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ በቀን ፡ በማታ አንተ ፡ ብቻ ፡ ትላንትም ፡ ዛሬም ፡ የሁሉ ፡ ጌታ የእስራኤል ፡ ታቦት ፡ ጠላቶች ፡ ማርከውት አማሌቅ ፡ መሃል ፡ ይቀመጥ ፡ ብለው አማልክት ፡ ሁሉ ፡ ሲሰባበሩ ዳጐን ፡ ሲወድቅ ፡ ሲናቅ ፡ ባገሩ የእስራኤል ፡ ታቦት ፡ በአሸናፊነት ፡ ገባ ፡ በክብሩ አዝ፦ በኃይል ፡ ቢሆን ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ ኃይል በክብር ፡ ቢሆን ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ ክቡር በስልጣን ፡ ቢሆን ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ ባለስልጣን እግዚአብሔር ፡ እግዚአብሔር ፡ ኃያል (4x)

