Gubae

ዘምራለው

Zemeralew

እንዳሻው ታሪኩ · ፩ መንገድ · 2014

አሉኝ ምላቸውን ትቼ ወጥቼ ጌታ እግዚአብሄርን ተስፋ አርጌ መች አሳፈረኝ መች አከሰረኝ ጽኑ መከታ በረከት ሆነኝ ውለታው ብዙ ወደር የለው ተስፋዬ ትምኪቴም ዛሬም ትምክህቴ እርሱ ነው ዘምራለሁ ለዚህ ጌታ አከብራለሁ ይሄን ጌታ ከአባትም በላይ አባት ሆኖ ከእናትም በላይ እናት ሆኖ ከወዳጅም በላይ ወዳጄ ሆኖ ከዘመድም በላይ ዘመድ ሆኖ( አኑሮኛል ያኖረኛል /2/ አመሰግነዋለሁ እባርከዋለሁ /2/ 2.በምድረበዳ ድጋፍ መመኪያዬ ጠላት ሲገፋኝ ብርቱ ጋሻዬ ስዝል ስንደክም የሚያበረታኝ የሚራራልኝ ኢየሱስ አለንኝ ውለታው ብዙ ወደር የለው መታመኛዬ ጌታዬ ነው 3.ያኔ በማለዳ በህጻንነቴ ስጮህ የሰማኝ እርዳታን ፈልጌ ርቦኝ ያበላኝ ጠምቶኝ ያጠጣኝ በባዶነቴ ሙላቴ ሆነኝ ዛሬም ድጋፌ መታመኛዬ አለኝ የምለው የሱስ ጌታዬ

እንዳሻው ታሪኩ · ሁሉም ዘማሪዎች