Gubae

ከሆነው ሁሉ

Kehonew Hulu

እንዳሻው ታሪኩ · ፩ መንገድ · 2014

ከሆነው በጎነት ከኔ ነው ምለው ምን አለ ከሆነው መልካምነት ከራሴ ምለው ምን አለ ያማረብኝ ባንተ ነው ሰው የሆንኩት ባንተ ነው መዳኔ ባንተ ነው በጎልጎታው ስራህ ነው 1. የበገና ቃና የዝማሪዬ ሚስጥር መቆሜ ባንተ ነው ማገልገሌ በቤትህ ልጅህም መባሌ በራሴ አይደለም በጸጋህ ነው እንጂ ከኔ ነው ምለው የለም ከአለም ርኩሰት ከእሳት ያመለጥኩት ባንተ ነው ዛሬ ላይ መቆሜ ምህረትህ በዝቶ ነው ባንተ ነው ከሆነው ሁሉ ከኔ ነው ምለው የለም/2/ ያማረብኝ ባንተ ነው ሰው የሆንኩት ባንተ ነው መዳኔ ባንተ ነው መትረፌ ባንተ ነው 2. ያለፈውን ሁሉ ቆም ብዬ ሳየው የትዝታን መዝገብ የኋሊት ስገልጠው እንደማንነቴ የት ነበርኩ ይሄኔ ግን ማይገባኝ ተገብቶኝ ቤትህ አለው ዛሬ እዳዬን በሻርከው ሞቴን በወሰድከው ባንተ ነው ድቅድቅ ጨለማዬን ገፈህ ባበራኀው ባንተ ነው ይቅርታህ ብዙ ነው ምህረትህ ሰፊ ነው ሰፊ ነው ስለበዛው ስጦታህ ስለበዛው ውለታህ አመሰግንሀለው ሁሉ ባንተ ካንተ ሁሉ ለአንተ ነው ላንተ ነው ክብር ክብር ክብር ክብር ላንተ ይሁን ላንተ ይሁን ለዘላለም

እንዳሻው ታሪኩ · ሁሉም ዘማሪዎች