ጌታ ነው ኢየሱስ
Gieta New Eyesus
እንዳሻው ታሪኩ · ፩ መንገድ · 2014
ከስሞች የበላይ ታላቅ ስም ያለው የሰላም አለቃ ኢየሱስ ጌታ ነው ድንቅ መካር ሀያል አምላክ የተባለው የዘላለም አባት ጌታዬ ልዩ ነው ይለያል ኢየሱስ /2/ ጌታ ነው ኢየሱስ /2/ 1.በክብር በሞገስ ለሆነው ገናና አምልኮ ውዳሴ ይብዛለት ምስጋና ለሀያላን ሀያል ለሌለው አምሳያ ይብዛለት እልልታ አሜን ሀሌሉያ (4) ሀሌ ሀሌሉያ አሜን ሀሌሉያ ይብዛለት ምስጋና ይደርደር በገና ይደመር ዝማሬ ይጨመር ውዳሴ /2/ ይብዛለት ይብዛለት ምስጋናዬ ይብዛለት /2/ ለየሱሴ ለአባቴ ይጨመር ይጨመር 2.ከድንግል ተጸንሶ ስጋን የለበሰው በድንቅ በተአምራት ሀይሉን የገለጠው ያስጨናቂውን ቀንበር ፈጽሞ የሰበረው ሲአልን ድል ነስቶ ባባቱ ቀኝ ያለው የሱስ ለየት ይላል፣ ምስጋና ይገባዋል ይብዛለት ምስጋና ይደርደር በገና ይደመር ዝማሬ ይጨመር ውዳሴ ይብዛለት ይብዛለት ምስጋናዬ ይብዛለት ለየሱሴ ለአባቴ ይጨመር ይጨመር /2)

