እንደ እግዚአብሔር
Ende Egziabhier
እንዳሻው ታሪኩ · ፩ መንገድ · 2014
የሰው ልጅ መግባቢያ የቌንቌው ብዛቱ በየጎሳው ያለው የባህል ይዘቱ የሰውነት ተፈጥሮ ሞገሱ ውበቱ የአፍንጫ ማሽተት የጆሮ መስማቱ የበረዶ መንጣት የጸሃይ ድምቀቱ የከዋክብት ብዛት የሰማይ ርቀቱ የአበቦች መዋብ የመብል ማርካቱ አቤት የአምላክ ስራ ግሩም ነው ፍጥረቱ እንደ እግዚአብሄር ዔረ ማን አለ እንደ እግዚአብሄር ዔረ ማንም የለም እንደ ኢየሱሴ ዔረ ማን አለ እንደ ኢየሱሴ ዔረ ማንም የለም በሰማይ በምድር የለም አልነበረም ደግሞም አይኖርም አአለወይ አአለወይ የየየለም የየየለም ማንም የለም እንደግዚአብሄር ያለ/2/ 2.ነገስታትም መጡ በታላላቅ ግርማ ነግሰውም አለፉ ሁሉም በየተራ ሃያላንም ጠፉ ጀግኖችም አረጁ ሁሉም እንደ ጥላ ታይተው ተሰወሩ በአለም ላይ ያለው ትንሹም ትልቁም አለመኖሩ ማርጀቱ ማለፉ አይቀርም በጊዜ አይወሰን ዘላለማዊ ነው እኔ እኔ ነኝ እንዳለ ሁሌም እርሱ ያው ነው እንደ እግዚአብሄር ዔረ ማን አለ እንደ እግዚአብሄር ዔረ ማንም የለም እንደ ኢየሱሴ ዔረ ማን አለ እንደ ኢየሱሴ ዔረ ማንም የለም በሰማይ በምድር የለም አልነበረም ደግሞም አይኖርም አአለወይ አአለወይ የየየለም የየየለም ማንም የለም እንደግዚአብሄር ያለ/2/

