Gubae

ክብርህ በእኔ ላይ ይሁን

Kebreh Benie Lay Yehun

እንዳልካቸው ሐዋዝ · ክብርህን አሳየኝ · 2014

ውኃን ፡ የተጠማ ፡ ሰው ሳይጠጣ ፡ እንደማይረካ እኔም ፡ ተጠምቼሃለሁ ክብርህን ፡ ሳይ ፡ ብቻ ፡ እጠግባለሁ (፪x) ክብርህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ይሁን (፪x) ኦ ፡ ክብርህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ይሁን (፪x) ሌላውማ ፡ አያጠግበኝ ፡ እኔን ሌላውማ ፡ አያረካው ፡ ልቤን (፪x) ሁሉን ፡ አየሁ ፡ ግን ፡ እንደአንተ ፡ የከበረ አላገኘሁ ፡ አላገኘሁ (፪x) ምን ፡ አለ ፡ በዚህ ፡ ምድር ፡ ላይ ፡ ከአንተ ፡ የሚወዳደር ልኖርለት ፡ የሚገባኝ ፡ ከክብርህ ፡ በስተቀር ሌላውማ ፡ አያጠግበኝ ፡ እኔን ሌላውማ ፡ አያረካው ፡ ልቤን (፪x) የባሕሪው ፡ ምሳሌ ፡ የክብሩ ፡ ነጸብራቅ ፡ የሆንከው ከአባትህ ፡ እቅፍ ፡ የወጣሀው ኢየሱስ ፡ የምሻው ፡ አንተን ፡ ነው (፫x) የእግዚአብሔር ፡ ክብር ፡ የምሻው ፡ አንተን ፡ ነው ኢየሱስ ፡ የምሻው ፡ አንተን ፡ ነው

እንዳልካቸው ሐዋዝ · ሁሉም ዘማሪዎች