ነፍሴን የሚያረካት
Nefsen Yemiyarekat
እንዳለ ወልደጊዮርጊስ · ምነው · 2022
ማን ፡ ተወኝ ፡ ማን ፡ ተቀየረ ፡ እያልኩኝ ፡ ሳዝን ፡ መኖሬ አብቅቷል ፡ ልቤ ፡ በርትቷል ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ስላለ ፡ ጐኔ የማንም ፡ ፊት ፡ እንደቀድሞ ፡ ባይሆን ፡ ከእኔ ፡ ጋር ሃሴት ፡ ከ'ኔ ፡ ጋር ፡ ነው ፡መሽቶ ፡ ሲነጋ ፡ ፪* ነፍሴን ፡ የሚያረካት ፡ ምሥጋና ፡ 'ሚሞላት ፡ ይሄ ፡ ነው ነፍሴን ፡ የሚያረካት ፡ አምልኮ፡ 'ሚሞላት ፡ ይሄ ፡ ነው የአንተ ፡ ፊት ፡ ተቀብሎኛል ፡ እጅህ ፡ አቅፎኛል <ጌታ ፡ ሆይ ፡በአንተ ፡ ደስ ፡ ይለኛል > ፡ ፰* ላይሰለጥንብኝ ፡ ልቤ ፡ ላይ ፡ ጨለማ ፈገግ ፡ ካለልኝ ፡ የአንተ ፡ ፊት ፡ ከበራ እረክታለች ፡ ነፍሴ ፡ በማትለወጠው ሁልጊዜ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ነው ፡ ማየው የበራልኝ ፡ ፊትህ ፈገግ ፡ ያለው ፡ ፊትህ ጨለማዬን ፡ አሸንፏል ጌታ ፡ በአንተ ፡ ደስተኛ ፡ ነኝ ነፍሴን ፡ የሚያረካት ፡ ምሥጋና ፡ 'ሚሞላት ፡ ይሄ ፡ ነው ነፍሴን ፡ የሚያረካት ፡ አምልኮ፡ 'ሚሞላት ፡ ይሄ ፡ ነው የአንተ ፡ ፊት ፡ ተቀብሎኛል ፡ እጅህ ፡ አቅፎኛል <ጌታ ፡ ሆይ ፡በአንተ ፡ ደስ ፡ ይለኛል > ፡ ፰* ማን ፡ ተወኝ ፡ ማን ፡ ተቀየረ ፡ እያልኩኝ ፡ ሳዝን ፡ መኖሬ አብቅቷል ፡ ልቤ ፡ በርትቷል ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ስላለ ፡ ጐኔ የማንም ፡ ፊት ፡ እንደቀድሞ ፡ ባይሆን ፡ ከእኔ ፡ ጋር ሃሴት ፡ ከ'ኔ ፡ ጋር ፡ ነው ፡መሽቶ ፡ ሲነጋ ፪*

