እግዚአብሔር ነው ብርሃኔ
Egziabeher New Brhane
እንዳለ ወልደጊዮርጊስ · ምነው · 2022
ጨለማዉ ከብርሃኔ በላይ አይደለም ህመሜ ከመድኃኒቴ በላይ አይደለም እግዚአብሔር ነው ብርሃኔ እግዚአብሔር ነው መድኃኒቴ እንዳልደናገር እንዳይገባይ ግራ አለ ብርሃኔ ፊቴን የሚመራ እህ ስል ሳቃስት ፈዉስን ፈልጌ ጤና የሚያደርገኝ የሚሆን መድኃኒቴ እግዚአብሔር ነዋ ብርሃኔ እግዚአብሔር ነዋ መድኃኒቴ ጨለማዉ ከብርሃኔ በላይ አይደለም ህመሜ ከመድኃኒቴ በላይ አይደለም እግዚአብሔር ነው ብርሃኔ እግዚአብሔር ነው መድኃኒቴ የሚያስፈራራኝ ክምሩ ጨለማ ሊያስብለኝ የሚሻ የዉድቀትን ዜማ ከፊቴ ተገፎ አምልጣለች ነፍሴ ዛሬም አምላኬ ነው ብርሃን ፈዉሴ እግዚአብሔር ነዋ ብርሃኔ እግዚአብሔር ነዋ መድሃኒቴ የምፈራው የማከብረው ብርሃኔን እንጂ ጨለማን አይደለም የምፈራው የማከብረው መድኃኒቴን እንጂ ህመሜን አይደለም የሚያስፈራ እግዚአብሔር ብቻ ሚያስደነግጥ እግዚአብሔር ብቻ ጨለማዉ ከብርሃኔ በላይ አይደለም ህመሜ ከመድኃኒቴ በላይ አይደለም እግዚአብሔር ነው ብርሃኔ እግዚአብሔር ነው መድኃኒቴ

