ኃይልህ በድካሜ ሲገለጥ
Hayleh Bedekamie Sigelet
ኤልያስ አብጤ · የሚጤስ ጧፌን አላጠፋም
አዝ፦ ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ በአንተ ፡ አለፍኩት ፡ ይህን ፡ ዘመኔን ፡ ይህን ፡ ኑሮዬን አገልግሎቴን ፡ መድኃኒቴ ክብር ፡ ይሁንህ ፡ ጉልበቴ ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ጠላቴን ፡ መታሁት ፡ አሸነፍኩት ፡ አዋረድኩት አሳፈርኩት ፡ መድኃኒቴ ክብር ፡ ይሁንህ ፡ ጉልበቴ ከባርነት ፡ ቤት ፡ ስታላቅቀኝ ቀንበሬን ፡ ሰብረህ ፡ ስትጥልልኝ ባህሩን ፡ በክንድህ ፡ ስትከፍልልኝ ጭቃው ፡ ሳይነካኝ ፡ ስታሻግረኝ ጫማዬ ፡ አልቆ ፡ በእግሬ ፡ ሳልሄድ ጨርቄም ፡ ከገላዬ ፡ ሳይቀደድ በበለዓም ፡ ፊት ፡ ሞገስ ፡ ለድንኳኔ አጎናጸፍከኝ ፡ ክበር ፡ መድህኔ ንገሥ ፡ መድህኔ አዝ፦ ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ በአንተ ፡ አለፍኩት ፡ ይህን ፡ ዘመኔን ፡ ይህን ፡ ኑሮዬን አገልግሎቴን ፡ መድኃኒቴ ክብር ፡ ይሁንህ ፡ ጉልበቴ ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ጠላቴን ፡ መታሁት ፡ አሸነፍኩት ፡ አዋረድኩት አሳፈርኩት ፡ መድኃኒቴ ክብር ፡ ይሁንህ ፡ ጉልበቴ ቆሜያለሁ ፡ ሚልን ፡ የሚያፍገመግም ብርቱ ፡ ነኝ ፡ ያለውን ፡ የሚያደክም ይሄ ፡ ክፉ ፡ ቀን ፡ ፍጹም ፡ ሲያሯሩጥ በወዳጁ ፡ ፊት ፡ ሲያለማምጥ ክረምትም ፡ በጋም ፡ ለማይሞላው ፡ ሆድ ሗላውን ፡ ሳያውቅ ፡ ሰው ፡ ሲካካድ ሁሉን ፡ አራግፋ ፡ ያየችህ ፡ ነፍሴን በድንቅ ፡ አኖርካት ፡ ክበር ፡ ኢየሱሴ ፡ ንገስ ፡ ኢየሱሴ አዝ፦ ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ በአንተ ፡ አለፍኩት ፡ ይህን ፡ ዘመኔን ፡ ይህን ፡ ኑሮዬን አገልግሎቴን ፡ መድኃኒቴ ክብር ፡ ይሁንህ ፡ ጉልበቴ ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ጠላቴን ፡ መታሁት ፡ አሸነፍኩት ፡ አዋረድኩት አሳፈርኩት ፡ መድኃኒቴ ክብር ፡ ይሁንህ ፡ ጉልበቴ ጉስቁልናዬን ፡ እያስቆጠረኝ ይሄ ፡ ጠላቴ ፡ ሲያስለቅሰኝ የቀራዮን ፡ ደም ፡ አንዳልዘነጋ አይኔን ፡ አቅንቼ ፡ አንተን ፡ ፍለጋ ጉስቁልናዬን ፡ በብልጽግና ከላይ ፡ ከአርያም ፡ ሞላህና ስት ፡ ሸላልመኝ ፡ እፍረት ፡ ሆነለት አበሳውንም ፡ አበዛህበት ጠላቴን ፡ ክበር ፡ የኔ ፡ አባት አዝ፦ ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ በአንተ ፡ አለፍኩት ፡ ይህን ፡ ዘመኔን ፡ ይህን ፡ ኑሮዬን አገልግሎቴን ፡ መድኃኒቴ ክብር ፡ ይሁንህ ፡ ጉልበቴ ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ጠላቴን ፡ መታሁት ፡ አሸነፍኩት ፡ አዋረድኩት አሳፈርኩት ፡ መድኃኒቴ ክብር ፡ ይሁንህ ፡ ጉልበቴ በአንዳንዱ ፡ ቀን ፡ ውስጤን ፡ ሲከፋው የነፍሴን ፡ ጓዳ ፡ ባዶ ፡ ነህ ፡ ሲለው መታጠቂያዬን ፡ ማጥበቅ ፡ ሲያቅተኝ ታናሽነቴ ፡ ሚናቅ ፡ ሲመስለኝ ደመናን ፡ ቀዶ ፡ ክንድህ ፡ ይወርዳል መወርወሪያውን ፡ ይቆራርጣል ሥራዬን ፡ ሰርተህ ፡ ስትዋጋልኝ እጆቼን ፡ በአፌ ፡ ላይ ፡ አስጫንከኝ ተመስገንልኝ አዝ፦ ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ በአንተ ፡ አለፍኩት ፡ ይህን ፡ ዘመኔን ፡ ይህን ፡ ኑሮዬን አገልግሎቴን ፡ መድኃኒቴ ክብር ፡ ይሁንህ ፡ ጉልበቴ ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ፡ ሲገለጥ ጠላቴን ፡ መታሁት ፡ አሸነፍኩት ፡ አዋረድኩት አሳፈርኩት ፡ መድኃኒቴ ክብር ፡ ይሁንህ ፡ ጉልበቴ

